Connect with us

አያት አደባባይ እና የሱሉልታ አካዳሚ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም ተሰየመ

አያት አደባባይ እና የሱሉልታ አካዳሚ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም ተሰየመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 

ስፖርት

አያት አደባባይ እና የሱሉልታ አካዳሚ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም ተሰየመ

አያት አደባባይ እና የሱሉልታ አካዳሚ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም ተሰየመ

~  350 ግራም ወርቅ እና ዘመናዊ መኪና ተሸልማለች፣

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  አያት ተብሎ የሚጠራውን አደባባይ በኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም እንዲሰየም እና አደባባዩን ለማልማት የ2 ሚሊዮን ብር መደበ።

ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ አገር አቀፍ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።

በእውቅና መርሐ ግብር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት ደራርቱ ቱሉ ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ ላበረከተችው አስተዋጽኦ የከተማ አስተዳደር አያት አደባባይ በስሟ እንዲሰየም መወሰኑን እና አደባባዩን ለማልማትም 2 ሚሊዮን ብር መመደቡን ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል ።

ትላንት ማምሻውን በተደረገ አገር አቀፍ የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በኦሊምፒክ እና በሌሎች ውድድር መድረኮች ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ላደረገችው ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሀገር አቀፍ የክብር የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶላታል።

የእለቱን የእውቅናና ምስጋና መርሀ ግብሩ አዘጋጆች 350 ግራም የወርቅ ኒሻን እንዲሁም 2020 ሞዴል ኔክሰስ መኪና ሸልማት አበርክተውላታል።

በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአዳማ የሚገኘውን ትልቁ አደባባይን በኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መሰየሙን ያስታወሱት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ በአንድ ቢሊዮን ብር የተገነባው የሱሉልታ አካዳሚንም በስሟ መሰየሙን አብስረዋል።

በመጨረሻም ከአቅም በላይ በሆነ በስራ ምክንያት በመርሀ ግብር ላይ በአካል መገኘት ያልቻሉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቪዲዮ ባስተላለፋት መልዕክት ደራርቱ ለሀገር ማድረግ የሚገባትን ሁሉ ያደረገች ጠንካራና የዓላማ ፅናት ምሳሌ መሆኗን ገልፀዋል።

በእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራሙ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች፣ አርቲስቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

 

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top