Connect with us

ጥቂት ምክር ~ ለብልፅግናዎች!

ጥቂት ምክር ~ ለብልፅግናዎች!

ነፃ ሃሳብ

ጥቂት ምክር ~ ለብልፅግናዎች!

ጥቂት ምክር ~ ለብልፅግናዎች!
(ጫሊ በላይነህ)

እንግዲህ በአዲስአበባ ከተማ በመዋቅር የታገዘ የመሬት ወረራ እና ለማይገባቸው ግለሰቦች የኮንደምኒየም ቤቶች የማደል ተግባር መፈፀሙን ኢዜማ በራሱ ተነሳሽነት ጥናት አካሂዶ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ችግሩ መኖሩ ቀደም ሲልም የሚታወቅና በተለይ በማህበራዊ ሚድያው ብዙ ሲባልበት የቆየ ነው። የአሁኑን ለየት የሚያደርገው በጥናት መረጋገጡ ብቻ ነው።

ይህ ተግባር ቀደም ሲል በአዲስአበባ ስለህዝብ ሰፈራ (ዲሞግራፊ ቅየራ) እቅዱን የተናገረው አቶ ለማ መገርሳ በቅርብ ደግሞ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተመሳሳይ ከተናገሩት ጋር የሚመጋገብ ነው።

የኢዜማ ጥናት ብልፅግና በአዲስአበባ ህዝብ ያለውን ቅቡልነት መናዱ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ለመምራት፣ ህግና ስርአትን ጭምር ለማስከበር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከባድ ቻሌንጅ ውስጥ የሚዘፍቅ ነው። የህዝብ አመኔታ ያጣ መንግስት ስራውን በአግባቡ ማከናወን ስለማይችል እድሜ ሊኖረውም አይችልም።

በዚህ ላይ የአዲስአበባ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑ እየተሰሩ የነበሩ ህገወጥ ተግባራትን ያውቃሉ ወደሚል ድምዳሜ ሊወስድ ይችላል።

ከምንም በላይ ደግሞ እንዲህ አይነት አይን ያወጡ ህገወጥ ተግባራት የራሱን የብልፅግናን ውስጣዊ አንድነት ሊንደው ይችላል።

እናም ብልፅግና ብልጥ ከሆነ ባይወደውም እንኳን በዚህ ህገወጥ ተግባር የተሳተፉ አመራሮችን አንድ በአንድ ለቅሞ ተጠያቂ በማድረግ ህገወጥ ተግባሩን እንደማይደግፍ ተግባራዊ ማረጋገጫ መስጠት አለበት። በተዘማሪም ለአስነዋሪ ጥፋቱም ህዝብን በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለበት።

እንደገናም በህገወጥ መንገድ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችና ቡድኖች የወሰዱትን የህዝብ መሬት እና የኮንደምኒየም ቤት እንዲመልሱ ማድረግ አለበት።

ሌላው አማራጭ ጉዳዩን በማቃለል ወይንም በማድበስበስ ሊያልፈው ከሞከረ የማይቀረውን የፓለቲካ ሞቱን ለመጎንጨት በቅድሚያ ራሱን ማዘጋጀት አለበት።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top