Connect with us

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ተፅእኖ

ቢሸፍቱ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ተፅእኖ የቀጣይ መፍትሔ አቅጣጫ ጉባኤን እያስተናገደች ነው

ኢኮኖሚ

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ተፅእኖ

ቢሸፍቱ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ተፅእኖ የቀጣይ መፍትሔ አቅጣጫ ጉባኤን እያስተናገደች ነው።
****
ኮቪድ 19 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያስከተለውን ተፅዕኖና በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረው ሀገራዊ ጉባኤ በቢሸፍቱ እየተካሄደ ነው።

ይህ ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን 2012 በቢሸፍቱ ከተማ ፒራሚድ ሆቴል የጀመረው ጉባኤ የክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ባለ ድርሻ አካላትና ጉዳዮ የሚመለከታቸው ተቋማት ታድመውበታል።

ጉባኤውን ያዘጋጀው የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ጥናቱ ኮቪድ 19 በሀገራችን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ያሳደረውን ጫና ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ ለማሳየት የተሰራ መሆኑን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ገልፀዋል።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳሁ የኮቪድ 19 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያሳደረውን ተፅእኖ ተጨባጭ በሆነ ጥናት ለማረጋገጥ የጥናት ቡድኑ አባላት በዚህ ከባድ ወቅት መስዕዋትነት ከፍለው ለሰሩት ስራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመድረኩ የኮቪድ 19 ተፅእኖ የቀረበ ሲሆን ለጥናቱ መነሻ የሆኑ መረጃዎቹ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተሰባሰበ ነው። በአቅራቢዎቹ በተገለጸው መሰረትም ከዚህ ቀደም መሰል ክስተቶች በግምት የሚገለፁ የጉዳት መጠኖችን በማስወገድ ለመንግስት፣ ለዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ለተመራማሪዎች ትክክለኛና ታማኝ መረጃ በመስጠት ከፍተኛ ጥቅም እንዲኖረው ታስቦ የተሰራ ነው። ጉባኤው በዛሬው ውሎ በቀረበው ጥናት ላይ ውይይት ያደርጋል ሲል የድሬ ቲዩብ ዘጋቢ ከስፍራው የላከው መረጃ ያመለክታል።
ፎቶው ከገዛህኝ አባተ የተገኘ ነው።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top