Connect with us

የትኩረት መዛባት!

የትኩረት መዛባት!
Photo: Social Media

ጥበብና ባህል

የትኩረት መዛባት!

የትኩረት መዛባት!

እዮብ ማሞ (ዶክተር)

ከእቅድህ ክልል ውጪ በሆነው ነገር ላይ ትኩረትህን በመጣል ዘመንህን አታቃጥል፡፡ በየእለቱ የምታሰላስለው፣ የምታየው፣ የምትመኘውና ስሜትህንና ጊዜህን የምታሳልፈበትን ነገር አስበው፡፡ ይህ ነገር በወደፊት እቅድህና ዓላማህ ውስጥ የተካተተ ነገር ካልሆነ ወይም ከዚያ ጋር ግንኙነት ከሌለው የትኩረት መዛባት ውስጥ ነው ያለኸው፡፡

ወደ አንድ አቅጣጫ ለመድረስ ዓላማን ይዞ ወደፊት የሚሄድ ሰው የትኩረቱ ቅኝትና የስሜቱ ግለት በዚያው አቅጣጫ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የሚገሰግሰው ወደፊት፣ የሚያየውና የሚመኘው ግን የጎንዮሽ ወይም ወደኋላ ከሆነ የትኩረት መዛባት አለ፡፡

ከእቅድህና ከዓላማህ ውጪ ስለሆነ የሕይወት ዘይቤ ሲያወጡና ሲያወርዱ መዋል . . . ልታገኛቸው የማትችላቸውንና በሕይወትህ ምንም መዋጮ ሊያደርጉ ስለማይችሉ ሰዎች ሁኔታ ሲደመሙ ውሎ ማደር . . . ካለህ ወቅታዊ እውነታም ሆነ ከወደፊት እቅድ ጋር በፍጹም ሊጣጣምና ሊዋሃድ በማይችል አለም ውስጥ በሃሳብ ሲዋዥቁ መኖር . . . የተዛባ ትኩረት!

ዓላማህን ለይተህ እወቅ . . . እውነታህን ተቀበል . . . ትኩረትህን በዚያ ላይ ሰብስብ . . . ሃሳብህን፣ ምኞትህን፣ ስሜትህንና ያለህን አቅም ሁሉ በዚያ ላይ አውለው! የሆንከውን፣ ያለህን ነገርና ሁለንተናህን አስተባብረህ ወደፊት በመገስገስና እደርስበታለሁ ብለህ በማመን ባላቀደከው ነገር ላይ አይንህንና ሃሳብህን በመትከል ጊዜህን አታባክን፡፡

የትኛው ንስር ነው ከፍታው ላይ መብረሩንና መናጠቁን ትቶ የሜዳ እንስሶችን ሩጫ ሲመኝ የሚውለው? የትኛው አንበሳ ነው ደኑን እየገዛና እያደነ ከመኖር ይልቅ በውሃ ዳር ሆኖ የአሳዎችን ዋና በማየትና በመመኘት ጊዜውን የሚያሳልፈው? . . . እነዚህ ምሳሌዎቻችን የወደፊታቸው በሌለበት ነገር ላይ ጊዜያቸውን አያባክኑም፡፡ ትኩረትህን ወደ ማንነትህና ወደነገው ዓላማህ መልስ!

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top