Connect with us

ዳግም ውልደት

ዳግም ውልደት
Photo: Social Media

አስገራሚ

ዳግም ውልደት

ንስር እስከ ሰባ ዓመት በሕይወት የመኖር ጸጋ ተሠጥቶታል። ነገር ግን ይህን የ70 ዓመት የዕድሜ ፀጋ አጣጥሞ ለመኖር አርባኛ ዓመቱ ላይ በሕይወቱ ወሳኝ የሚባል ውሳኔ ማሳለፍ ይጠበቅበታል። ይኸውም ንስሩ አርባኛ ዓመት ዕድሜው ላይ እረዥምና እንደልብ የሚተጣጠፉት ጥፍሮቹ እንደ እንጨት ይገተራሉ።

ስል የነበረው ማቁርቱም ወደ አንገቱ ይታጠፍና ምግቡን አንድኖ እንዳይዝ ያግደዋል። ያረጁ ላባዎቹም ከደረቱ ላይ ተጣብቀው የመብረር ስራውን አስቸጋሪ ያደርጉበታል። በዚህ ወቅት ንስሩ ሁለት ወሳኝ አማራጮች ይጠብቁታል።አንድም ሞትን አሜን ብሎ መቀበል ወይም ደግሞ አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት (5 ወር) የሚፈጅ ፈታኝ የለውጥ ሂደት ማካሄድ።
በለውጡ ሂደት ለማለፍ ከወሰነ ቀጣዮችን ተግባራት መፈጸም ይጀምራል።

በመጀመሪያ ንስሩ ከፍ ካለ ተራራ በመውጣት ጎጆውን ይቀልሳል። ከዚያም ተራራው አለት ላይ ይቀመጥና የታጠፈውን ማንቁርቱንና ጥፍሮቹን ከአለቱ ጋር ደጋግሞ በመምታት ወልቀው እንዲወድቁ ያደርጋል። በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የህመም ስሜት አለው። አዲስ ማንቁርት እስኪያበቅል ምግብ አይበላም። የገረረውና የታጠፈውን ማንቁርት እንዲሁም ጥፍሮቹን አውልቆ ከጣለ በኋላ ከስር የወጣው ሙሽራ ማንቁርትና ጥፍር እስኪጠነክር ድረስ ለቀናቶች ይታገሳል።

ማቁርቱና ጥፍሮቹ ከጠነከሩ በኋላ ቀጣይ የሚጠብቀው ተግባር የደረቁትና ከደረቱ ጋር ተጣብቀው ከመብረር ያገዱትን ላባዎች እየነጨ በማራገፍ በአዲስ እንዲተኩ ማድረግ ነው። ይህን እልህ አስጨራሽና አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት የፈጀውን የለውጥ ጉዞ ከአካሄደ በኋላ ዳግም ውልደቱን በማወጅ ቀጣይ ሰላሳ ዓመታትን በትኩስ ኃይል ለመኖር አሀዱ ብሎ መብረር ይጀም ራል።

አዲስ ዘመን ግንቦት 16/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top