Connect with us

ኢዜማ በአዲስ አበባ የሚታየውን የመሬት ወረራ ተጨባጭ መረጃ ይፋ ሊያደርግ ነው

ኢዜማ በአዲስ አበባ የሚታየውን የመሬት ወረራ ተጨባጭ መረጃ ይፋ ሊያደርግ ነው
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

ኢዜማ በአዲስ አበባ የሚታየውን የመሬት ወረራ ተጨባጭ መረጃ ይፋ ሊያደርግ ነው

ኢዜማ በአዲስ አበባ የሚታየውን የመሬት ወረራ ተጨባጭ መረጃ ይፋ ሊያደርግ ነው

~ የከተማ አስተዳደሩን ማብራሪያ ጠይቋል፣

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የመሬት ወረራን በማስመልከት ምላሽ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠየቀ፡፡

ኢዜማ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት በላከው ደብዳቤ ላይ ከብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የተውጣጣ ኮሚቴ አዋቅሮ ላለፉት ሁለት ወራት የመሬት ወረራን በሚመለከት የማጣራት ሥራ ሲሠራ እንደነበር ገልጿል፡፡ በማጣራት ሥራውም የተለያዩ የጽሑፍ፣ የፎቶ ግራፍ እና የቪዲዮ መረጃዎች እና ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ጠቁሞ፤ ባካሄደው የመስክ ጉብኝትም የችግሩን ስፋት ለማረጋገጥ እንደቻለ አስታውቋል፡፡

ኢዜማ፣ የመሬት ወረራውን አሳሳቢነትና ሕገ ወጥ አሠራር በተመለከተ በመረጃ እና በማስረጃ አስደግፎ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በደብዳቤው ላይ የገለፀ ሲሆን ከደብዳቤው ጋር ባለ 3 ገጽ አባሪ በማድረግ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት በላከው የጥናቱ ጭምቅ ሀሳብ ላይ ጽሕፈት ቤቱ በሶስት ቀናት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ ጋር የተያያዙ ችግሮች በማስመልከት ኮሚቴ አቋቁሞ ላለፉት ሁለት ወራት ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች መረጃዎችና ማስረጃዎችን ሲሰበስብ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ፓርቲው ሲያሰባስበው በቆየው መረጃዎችና ማስረጃዎች የደረሰበትን ውጤት በቀጣይ ሳምንት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top