Connect with us

የአዲስአበባ ከተማ የመሬት ወረራ፣ የኮንደሚኒየም፣ የቀበሌ ቤቶች ጉድ

የአዲስአበባ ከተማ የመሬት ወረራ፣ የኮንደሚኒየም፣ የቀበሌ ቤቶች ጉድ
Photo: Social media

ዜና

የአዲስአበባ ከተማ የመሬት ወረራ፣ የኮንደሚኒየም፣ የቀበሌ ቤቶች ጉድ

የአዲስአበባ ከተማ የመሬት ወረራ፣ የኮንደሚኒየም፣ የቀበሌ ቤቶች ጉድ

– 322 ባለቤት አልባ ሕንጻዎች ተገኝተዋል፣

– 32 ሺ የኮንደሚኒየም ባለቤቶች ቤቶቹ እንዴት እንያዙት አይታወቅም፣

– ከ75 በመቶ በላይ ቤት የደረሳቸው ሰዎች በቤት ውስጥ አይኖሩም፣

(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ባካሄደው ጥናት መሰረት 322 ባለቤት አልባ ሕንጻዎች መገኘታቸውን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ባለቤት አልባ ቤቶቹበሕጋዊ መንገድ የተሰጠባቸው መረጃ እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ መረጃ አለመገኘቱን ጠቅሰው ባለቤቶቹ እጅ መረጃ ይገኝ እንደሆን በተደጋጋሚ ለአንድ ወር ያህል ማስታወቂያ ተለጥፎ ባለቤት ነኝ የሚል መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡ 

ቤቶቹ በጠቅላላው 229 ሺ 556 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉና እያንዳንዳቸው ከ500 ካሬ ሜትር በላይ ቦታ የያዙ ናቸው፡፡ ሕጻዎቹ በተለያየ ደረጃ እንደሚገኙና ከእነዚህ መካከል 18 የተጠናቀቁ፣ 264 ያህል በተለያዩ ደረጃዎች እንደሚገኙ አንዳንዶቹ ከለውጡ ወዲህ ግንባታቸው መቋረጡን በጥናቱ መለየቱን ጠቅሰዋል፡፡

13ኛ ዙር ሳይጨምር ከ 177 ሺ በላይ የኮንደሚኒየም ቤቶች ለተጠቃሚዎች መተላለፉን የጠቀሱት ከንቲባዋ ከእነዚህ መካከል 32 ሺ ያህሉ እንዴት እንደተላለፈላቸው እንደማይታወቅ በጥናት መረጋገጡን ጠቅሰዋል፡፡ 

15 ሺ 891 ያህሉ ደግሞ ምንም ኣይነት ሕጋዊ ማስረጃ የላቸውም ብለዋል፡፡ 4 ሺ 30 ያህል ለረዥም ጊዜ ዝግ መሆናቸውን የጠቀሱት ከንቲባዋ ቤቶቹ የተዘጉበት ጊዜ ከ2 እስከ 10 ዓመት እንደሚደርስ ጠቅሰዋል፡፡ 850 የኮንደሚኒየም ቤቶች ጨርሶ ሰው ገብቶባቸው የማያውቅ  ሲሆኑ 424 ቤቶች በግለሰቦች ተሰብረው የተገባባቸው መሆናቸው መረጋገጡን አስታውቀዋል፡፡

ከአጠቃላይ የኮንደሚኒየም ቤቶች 75 በመቶ ያህሉ ዕጣው የደረሳቸው ባለቤቶች እየኖሩበት አይደለም ያሉት ከንቲባዋ ቤቶች ወይ በኪራይ ወይንም በሽያጭ ለሌላ ሶስተኛ ወገን መተላለፋቸውን እና መንግስት በድጎማ ለዝቅተኛው ህብረተሰብ ጥቅም የሰራቸው ቤቶች ባልተገባ ሁኔታ መገኘታቸውን አስረድተዋል፡፡

13ኛ ዙር ዕጣ የወጣላቸው በተመለከተ በጠቅላላው  51 ሺ 229 ዕጣ መውጣቱን፣ 22 ሺ 915 ገደማ ለአርሶአደሮች መሰጠቱን፣ ለአመራሩ፣ ለልማት ተነሺዎች የተሰጡ ቤቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

የቀበሌና የንግድ ቤቶችን በተመለከተ በጠቅላላው 138 ሺ 652 ቤቶች መኖራቸውን ከእነዚህ ውስጥ 7 ሺ723 ያህል ያለማስረጃ እየኖሩበት መሆኑን፣ 265 ቤቶች ለሶስተኛ ወገን መተላለፋቸውን፣ 1 ሺ 164 ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ኮንደሚኒየም ደርሷቸው ቤቶች አለመልቀቃቸውን፣ 1ሺ 243 በፍርድ ቤት እንዲታሸጉ የተደረጉ ሲሆን 180 ቤቶች በቦታቸው አለመገኘታቸውን ወይንም መጥፋታቸውን ተናግረዋል፡፡

ችግሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ሳይሆን በተለይ በ1997 ኣ.ም በከፍተኛ ደረጃ የመሬት ወረራ መታየቱን በማስታወስ ችግሩ የቆየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ የጥናት ግኝት መሰረት በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች ይህ ሁሉ ሲፈጠር ምን ሲሰሩ ነበር በሚል ተጠያቂነትን ለማስፈን ጉዳዩ ለፖሊስና ለአቃቤ ሕግ መተላለፉን እንዲሁም በአስተዳደራዊ እርምጃ መሬት ወደመሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉን ጠቅሰው የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የታየው ችግር በማረም ለረዥም ጊዜ ዕጣ ሲጠባበቁ ለነበሩ ወገኖቹ ቤቶቹ እንዲተላለፉ በአስተዳደሩ ካቢኔ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top