Connect with us

በጉባ ወረዳ አለመረጋጋት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 121 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጉባ ወረዳ አለመረጋጋት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 121 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

በጉባ ወረዳ አለመረጋጋት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 121 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ የብሔር ግጭትና አለመረጋጋት ለመፍጠር አልሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ቡድን አካል ናቸው የተባሉ 121 ተጠርጣሪዎችና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ ሀምደኒል እንዳስታወቁት የጥፋት ቡድኑ በጦር መሳሪያ በመታገዝ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት 2፡30 አካባቢ በጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ የ13 ንጹኃን ዜጎችን ሕይወት ቀጥፏል፡፡

ቡድኑ የብሔር ግጭት ለመፍጠር፣ አካባቢው የሕዳሴ ግድብ መገኛ መሆኑን ተከትሎ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በዚህም እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር ትልቅ ጥፋት የመፍጠር ዓላማ ያለው ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

“በተለይም አሁን ሀገርን እየመራ ያለው ፓርቲም ሆነ ለውጡ እኛን አይወክለንም” በማለት ወጣቱንና ሕዝቡን ለአመጽ የሚቀሰቅሰው ቡድን በክልሉ ከሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ትልቅ የጥፋት ቅንጅትና ተገቢ ድጋፍ እንደሚያገኝም ነው ኮሚሽነር መሀመድ ያስታወቁት፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ወጣቶችን በመመልመል፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር መከላከያ እና ከመንግስት የጸጥታ ሥራ የተቀነሱ ግለሰቦችን በመያዝ በሱዳን ድንበር አካባቢ አቡልታ በተባለ ቦታ በአማርኛ፣ በጉሙዝኛ እና በዓረብኛ ቋንቋዎች የጥፋት ስልጠና ሲሰጥ እንደነበር በተካሄደ ዘመቻ ወቅት መረጋገጡንና አስረጂ መረጃዎች መገኘታቸውንም አብራርተዋል፡፡

በተለይም በለውጥ ላይ በምትገኘው የሀገሪቱ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ያኮረፈው ህወሃት በአካባቢው በኢንቨስትመንት ስም የሚገኙ ባለሃብቶችን በመጠቀም ቡድኑ ለያዘው የጥፋት ተልዕኮ መሳካት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር አመላክተዋል፡፡

የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከሀገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን በጥፋት ቡድኑ ላይ ባደረገው ዘመቻም በቀጥታ የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ በነሩበት ወቅት የተያዙትን 61 ግለሰቦች ጨምሮ፣ የሎጅስቲክስ፣ የምግብና ሌሎች ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ እና በመንግስት ኃላፊነት የነበሩ ነገር ግን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ በድምሩ 121 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከግለሰቦቹ ጋርም ቡድኑ ሲጠቀምባቸው የነበሩ 1 አር ቢ ጂ የተባለ የቡድን የጦር ማሳሪያ ከ3 አቀጣጣይ እና 1 ቅምቡላ ጋር፣ 6 ክላሽ፣ 17 ኋላቀር የጦር መሳሪያዎች እንዲሁም 293 የብሬን እና 30 የክላሽ በድምሩ 223 የጥይት ፍሬ መያዙን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ ለተለያዩ ተልዕኮ ማስፈጸሚያነት ሲጠቀምባቸው ነበሩ 6 የሞተር ሳይክሎች እና ምግብ ዱቄት ተይዟልም ነው ያሉት፡፡

አሁን በአካባቢው አንጻራዊ ሠላም መኖሩን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ እየተወሰደ ያለውን የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ ውጤታማ ለማድረግ ህብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኤፍቢሲ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top