Connect with us

የቤንሻንጉል ክልል፤ የፌደራል መንግሥት ፅንፈኛ ያላቸውን ሀይሎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ

የቤንሻንጉል ክልል፤ የፌደራል መንግሥት ፅንፈኛ ያላቸውን ሀይሎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ
የቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት

ዜና

የቤንሻንጉል ክልል፤ የፌደራል መንግሥት ፅንፈኛ ያላቸውን ሀይሎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ

የቤንሻንጉል ክልል፤ የፌደራል መንግሥት ፅንፈኛ ያላቸውን ሀይሎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ

(የክልሉ መግለጫ እነሆ)

በሀገራች ኢትዮጵያ ከለውጡ ማግሥት አንስቶ የህዝቦችን ፍትሃዊ የልማት፣ የሠላምና የዴሞክራሲ ሥርዓት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሪፎርሞችን በማካሄድ ትርጉም ያላቸው ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ 

መላ የሀገራችን ህዝቦች የለውጥ ኃይሉ ተጨማሪ ስኬቶችን በማስመዝገብ ባጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ብልፅግና ማማ እንደሚያሻግሩት ብሩኅ ተስፋ ሰንቆ ያልተገደበ ድጋፉን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በአንፃሩ በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች ሲከሰቱ በሰከነ መንገድ ተወያይቶ ዘላቂነት ያለው የጋራ መፍትሄ መስጠት ሲገባ የውጭ ኃይሎችና የውስጥ ተባባሪዎቻቸው ወደ ባሰ ውጥንቅጥ እና የቀውስ አዙሪት ውስጥ ሊከቱን ጥረት ማድረግ ጀምረዋል፡፡

በእርግጥ ክልላችንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዜጎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ አስከፊ ድርጊቶች የሚወገዙና የድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ የመውሰዱ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ  የተለያዩ ፅንፈኛ ኃይሎች ሀገራችንን ወደ ባሰ ቀውስ እና ወደተወሳሰብ ችግር ውስጥ ለመክተት የሚያደርጉትን ጥረት በጥብቅ ማውገዝ፣ እሣትና ቤንዚን የሚያቀብሉትንም በአንድ ስሜት መቃወም  ከሁላችን የሚጠበቅ ወቅታዊ ሀገራዊ ኃላፊነት ይሆናል፡፡ 

የክልላችን መንግሥት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ቡድኖች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ በማስቀጠል የአካባቢውን ሠላም በዘላቂነት ከማረጋገጥ ባሻገር 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነትን ያገኘ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣ ያረጋግጣል። 

መላው የክልሉ ህዝብ የፅንፈኛ ኃይሎችን ፅንፍ የረገጠ ዕንቅስቃሴ አጥብቆ በመቃወም የሀገራችንን ህልውና ጠብቆ ለማስቀጠል ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 

ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግሥት አካላትም ተገቢውን ህጋዊ ዕርምጃ በመውሰድ  ፅንፈኛ ኃይሎች የሚያራምዱትን የጥፋትና የብጥብጥ አጀንዳ ሥርዓት እንዲያስይዙ ጥያቀውን ያቀርባል፡፡ 

የቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት

ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም

አሶሳ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top