Connect with us

“በኮንሶ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሽፋን ተከስቶ የነበረ ሁከት ከሸፈ” ፖሊስ

"በኮንሶ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሽፋን ተከስቶ የነበረ ሁከት ከሸፈ" ፖሊስ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“በኮንሶ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሽፋን ተከስቶ የነበረ ሁከት ከሸፈ” ፖሊስ

በኮንሶ ዞን እና በአሌ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሽፋን ፀረ ሰላም ሀይሎች ባስነሱት ሁከት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ውድመት ቢደርስም የዞኑ ፖሊስ ከክልሉ የፀጥታ ሀይልና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት በመስራቱ የአደጋውን መጠን በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የኮንሶ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሰለሞን ገመቹ ገልጸዋል፡፡

ሰሞኑን በአካባቢው የተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ የፀረ-ሰላም ሀይሎች ሴራ መሆኑን ለፖሊስና ርምጃው ጋዜጣ የገለጹት ምክትል ኮማንደር ሰለሞን ገመቹ የፀረ-ሰላም ሀይሎች በፈጠሩት ችግር የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን፣ በ9 ሰው ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም 528 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንና ከ3ሺ 5መቶ ሰዎች በላይ መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡

የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሽፋን በማድረግ የተቀሰቀሰው ሁከት ከክልሉ አልፎ የሀገሪቷን ሰላም በማወክ እንደ ችቦ ለማቀጣጠል የታቀደ ሴራ ቢሆንም ከታሰበው እቅድ አንፃር የፀጥታ ሀይሉ እና ማህበረሰቡ በእንጭጩ መግታታቸውንም ምክትል ኮማንደር ሰለሞን ገልፀዋል፡፡

ሀላፊው አያይዘውም በዞኑና በአሌ ወረዳ በሙስና እና በመልካም አስተዳደር ችግር የተቀነሱ አመራሮች የፀረ-ሰላም ሀይሎች ደጋፊ በመሆን የአካባቢው ፈተና ቢሆኑም በአሁኑ ሰዓት የዞኑ ፖሊስ፣የክልሉ ልዩ ሀይል፣ የፌደራልና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ በመሆን የህግ ማስከበር ስራ በተጠናከረ መንገድ በመስራታቸው የአካባቢው ማህበረሰብ የተለመደውን የዘወትር እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የተፈናቀሉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ወደ ቀያቸው ለመመለስ የኮንሶ ዞን እና የአሌ ወረዳ አመራሮች የሁለቱ ህዝቦች የሀገር ሽማግሌዎችን እና የሀይማኖት አባቶችን በማወያየት ጸጥታው ይበልጥ እንዲጠናከር እየሰሩ ነውም ብለዋል፡፡(የፌ/ፖሊስ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top