Connect with us

ኢትዮጵያዊው አፋር በአዋሽ ወንዝ ሙላት አደጋ ገጥሞታል

ኢትዮጵያዊው አፋር በአዋሽ ወንዝ ሙላት አደጋ ገጥሞታል
Photo: Social Media

ትንታኔ

ኢትዮጵያዊው አፋር በአዋሽ ወንዝ ሙላት አደጋ ገጥሞታል

ኢትዮጵያዊው አፋር በአዋሽ ወንዝ ሙላት አደጋ ገጥሞታል፡፡
በታችኛው አዋሽ የደረሰው የጎርፍ አደጋ ብዙ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

በክረምቱ እየጣለ ያለውን ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው ጎርፍና ከግድቦች የሚለቀቀው ውሃ መጠን መጨመር የአዋሽ ወንዝ በከፍተኛ ደረጃ እንዲሞላ ያደረገው ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በታችኛው አዋሽ አካባቢዎች ከፍተኛ አደጋ መከሰቱን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም ዞን አንድ በሚባለው አካባቢ በዱብቲና የሱልጣኔቶቹ ቀደምት መዲና በሆነችው አሳኢታ የደረሰው የጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ ጉዳዮን በተመለከተ የአፋር ክልል የማህበረሰብ አንቂዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እንደገለጹት ችግሩ በተደጋጋሚ አዋሽ በሞላ ቁጥር የሚከሰትና አስቀድሞ በአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን በኩል የሚሰሩ ስራዎች ደካማነት ውጤት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የድሬቲዩብ ምንጮች ከስፍራው ያነጋገሯቸው የአካባቢ ነዋሪዎች ደግሞ በፌዴራሉም በክልሉ መንግስትም እየተደረገ ያለው ድጋፍ የችግሩን መጠን ያህል አይደለም ብዙ የሚቀረውና ለተጎዱት ዜጎች ልንደርስላቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ አመት አዋሽና ግቤ ወንዞች ላይ የሚገኙ ግድቦች በጎርፉ መጠን መጨመር ሳቢያ የውሃ መልቀቅ ስራ ስለሚሰራ ከወንዞቹ በታች ያሉ አካባቢዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲሉ ጉዳዮ የሚመለከታቸው የስጋት ኮሚሽንና ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ቅድመ ጥንቃቄ መረጃ የሰጡ ቢሆንም ዜጎች ችግሩን በሚሻገሩበት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች አናሳ በመሆናቸው አሁንም በፍጥነት ሊደረስላቸው ይገባል፡፡ የዚህን ዜና ፎቶ ያገኘነው ከአሎ ያዮ ገጽ ነው፡፡

Continue Reading
Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top