Connect with us

ሰውየው ለምንድነው የጠመዱን?

ሰውየው ለምንድነው የጠመዱን?
Photo: Social Media

አለም አቀፍ

ሰውየው ለምንድነው የጠመዱን?

ሰውየው ለምንድነው የጠመዱን ?
(ዮሐንስ መኮንን)

የሕዳሴውን ግድብ ድርድር በተመለከተ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለብሉምበርግ በኢሜይል ግራ አጋቢ የሆነ መልእክት ልካለች። አሜሪካ ለብሉምበርግ በላከችው ኢሜይል፤

• ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ጊዜ እያለቀባት ነው!

• ለስምምነት የቀረው ጊዜ አጭር ነው። ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለው ዕድልም እየጠበበ መጥቷል።

• ሦስቱ ሀገሮች ቀናዒነቱ ካላቸው ግን፣ ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ አደጋች አይደለም።

በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል የሕዳሴው ግድብ የውኃ አሞላል መርኆዎች ላይ ሲካሄድ በቆየው የሦስትዮሽ ድርድር አሜሪካ “በታዛቢነት አሳትፉኝ” ብላ አንገቷን አስገብታ ራሷን ወደ “አደራዳሪነት” ከማሳደጓም በላይ ኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚያሳድር የ”መግባቢያ” ሠነድ ለማስፈረም ያደረገችውን ሙከራ የኢትዮጵያ ተዳራዳሪዎች ረግጠው መውጣታቸው ይታወሳል።

ዛሬ አሜሪካ ለብሉምበርግ በላከችው ማስጠንቀቂያ አዘል ኢሜይል ውስጥ ጥያቄዎች የሚያጭሩ ሃሳቦች አሉበት።

1. አሜሪካ የትኛውን ጊዜ ነው “እያለቀ ነው” ያለችው?

2. አሜሪካን ማን “ዓቃቤ ሰአት” አድርጎ ሾማት?

3. አሜሪካ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ፍላጎቷ ምንድነው?

ከሳምንት በፊት የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር በዓባይ ግድብ ምክንያት አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ በከፊል ለማቆም እየታሰበበት መሆኑን ፎሬን ፖሊሲ ድረገጽ መዘገቡ ይታወሳል።

ሰውየው (አቶ ትራምፕ) ግን ምን ነክቷቸዋል? “ምን አድርገናቸው ነው የጠመዱን” አያስብልም? ያን መከረኛ የኖቤል ሽልማት ዶ/ር ዐብይ በማሸነፋቸው የገባቸው ብስጭት አሁንም አልበረደላቸውም ማለት ነው?

(የብሉምበርግን ዘገባ ተመልከቱት)

 

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top