Connect with us

የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር) ከጠጡ በኋላ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር) ከጠጡ በኋላ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ
A man rides his bicycle past a graffiti on a road, amidst the spread of the coronavirus disease (COVID-19), in New Delhi, India, July 17, 2020. (REUTERS/Adnan Abidi)

አለም አቀፍ

የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር) ከጠጡ በኋላ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በህንዷ ከተማ ከአልኮሆል የተዘጋጀ የእጅ ማፅጃ (ሳኒታይዘር) ከጠጡ በኋላ በትንሹ የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

የህንዷ ኩሪቼዱ አንድራ ፕራዴሽ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑት በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት አልኮሆል ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ሟቾች በአልኮሆል ምትክ ሳኒታይዘሩን እንደጠጡት ስካይ ኒውስን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የአልኮሆል ሱሰኛ የሆኑ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘርን እንደ አልኮሆል እንደሚጠቀሙ ከፍተኛ የፖሊስ ሃላፊ ሲድሃርት ካውሻል ተናግረዋል፡፡

የፖሊስ ሃላፊው“የእንቅስቃሴ ገደቦች በመጣላቸው አልኮሆል አይገኝም፤ነገር ግን የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘሩ በቀላሉ ስለሚያገኝ እሱን ተጠቅመው ነው ለሞት የተዳረጉት ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሌሎች ሳኒታይዘሩን የጠጡ ሰዎች የሕክምና ክትትል አድርገው ከሆስፒታል መውጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ህንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቁ ሀገራት ከአሜሪካ እና ብራዚል በመቀጠል ሶስተኛ ነች፡፡

በሀገሪቱ እስካሁን ከ1 ሚሊዮን 7 መቶ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 37 ሺህ 436 የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top