Connect with us

ደግሞ አፍሪካ ህብረትን ነፍጠኛ በሉት

ደግሞ አፍሪካ ህብረትን ነፍጠኛ በሉት፤
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

ደግሞ አፍሪካ ህብረትን ነፍጠኛ በሉት

ለጣይቱ ልባቸውን የሚነፍጓት አይገርሙኝም እሷ ሰፊ ናት ጥቁር ህዝብ ልብ ላይ አርፋለችና የመንደር ልብ ይጠባታል፡፡
ደግሞ አፍሪካ ህብረትን ነፍጠኛ በሉት፤
ከስናፍቅሽ አዲስ

ጣይቱ ብርሃን ናት ለአፍሪካ ያበራች ብርሃን አፍሪካ ህብረት አፍሪካዊ ብርሃን በመሆኗ ክብር ቸሯታል፡፡ ሴትየዋ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ የተባለችው ሀገር አጨልማ አይደለም ሀገር አብርታ ነው፡፡ ያጨለመችው የቅኝ ገዢ ሻማ ነው፡፡

እቴጌ ከጎጃም ከጎንደር ከስሜን ትወለዳለች፡፡ እንደ እኔ ክብር የሚቸሯት አጥንት አይቆጥሩም፡፡ ሊያጥላሉ የሚሞክሩትም ቢሆኑ አጥንታቸው ከጣይቱ የሚርቅ አይደለም ምክንያቱም እሷ የወረሴህ የጁ ኦሮሞም ናት፡፡

ጣይቱን ማንሳት ክብር ማጣት የሚመስላቸው ጣይቱን ማክበር እንደሚያስከብር ከአፍሪካ ህብረት ቢማሩበት መልካም ነው፡፡ እንዲህም ሆኖ ህብረቱ ነፍጠኛ ነው የሚል የመንደር ጉድ አንወጣም፡፡ ጣይቱ የጋራችን ናት ለጋራ ሀገራችን ለጋራ ክብራችን ለጋራ ስማችን ምልክት ስለሆነች፡፡

አፍሪካ ህብረት አፍሪካውያን ሴቶችን ዘክሮ ክብር ሰጥቷል፡፡ ቅኝ መገዛትን ለቅኝ ግዛት እንቢኝ ማለትንና አለመገዛትን ጠንቅቀው የሚያውቁት ወንድሞቻችን ጣይቱን ምልክትም ክብርም ቢያደርጓት አያስደንቅም፡፡

እኛ ታመናል ህመማችን ብሷል ጣይቱን መጥላት ራሱን መውደድ የመሰለው ሞኝ በዚህ ዘመን አይተናል፡፡ ራስን መውደድ መገዛትን ባርነትን ሀገር አልባነትን ቋንቋ አልባነትን መውደድ ነው፡፡ እቴጌይቱ የዚህ ምልክት ናት፡፡

ጣይቱ በኢትዮጵያ ከተነሱ ታላላቅ ሴቶች አንዷ ብቻ አይደለችም፡፡ የጦር መካሪ፣ የአዳዲስ ፈጠራዎች አራማጅ የሀገር አቅኚ በመሆን ትልቃለች፡፡ ጣይቱ ለመጨረሻ ጊዜ ሌላውን የመግዛትና ሀገር የመውረርን ምኞት ያመከነች የሴት ጀግና ናት፡፡

ጣይቱ የአድዋ ምልክት ናት፤ የአድዋን ታሪክ ተጋርቶ ባለቤት መሆን ትውልድ የአባቶቹን ድርሻ መውሰድ ነው፤ አድዋን ንቆ ማጥላላት ትውልድ በአባቶቹ የሰማዕትነት ዋጋ መቀለድ ነው፡፡ ጣይቱ ራሷ አድዋ፣ አምባላጌ፣ እንዳመቂ ናት፡፡

የአፍሪካ ህብረት ልክ የሆነውን አድርጓል፡፡ ዛሬ በአስተሳሰብ፣ በስልጣኔ፣ በኑሮ ዘይቤ ቅኝ ለምትገዛውና ልትጠፋ ለተቃረበችው ምዕራብ ናፋቂ አህጉር የጣይቱ አይነት ሴቶች የኔን አይነት አፍሪካዊ የልብ ወኔ ያነሳሱታል፡፡ እምቢ ማለትን ያስተምሩታል፡፡ ነጻ መውጣትን ይሰብኩታል ጣይቱ የነጻ መውጣት ምልክት ናትና፤

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top