Connect with us

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ
FBC

ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩን በጽህፈት ቤታቸው ነው ተቀብለው ያነጋገሩት፡፡

ከልዑካኑ መካከል የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንT ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጆኣኪም ቺሳኖ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኪጋሌማ ሞትላንቴ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የአፍሪካ ህብረት ልዑካን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩ በአፍሪካዊ ወንድማማች መንፈስ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦት መምጣቱን አድንቀዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም ለሁለት ዓመታት ያህል ህወሓት ሃገሪቷን ለማተራመስ የሄደበትን ርቀትና መንግስት ያሳየውን ያላሰለሰ ሆደ ሰፊነት ለልዑካኑ አስረድተዋል፡፡

ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ መንግስት ህግ የማስከበር ዘመቻውን መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህግ የማስከበር ዘመቻው ንጹኀን በማይጎዱበት መልኩ በጥንቃቄ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚየስተባብር እና የሚመለከት ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱንም ለልዑካኑ አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም የሰላም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አውስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከቀያቸው የተሰደዱ ተፈናቃዮችን ተቀብሎ ለማቋቋም አራት መቆያዎች ተዘጋጅተዋልም ነው ያሉት፡፡

በትግራይ ክልል ህግን የተከተለ አስተዳደር እንደሚቋቋም ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥፋት ቡድኑ ያወደማቸው መሰረት ልማቶችን መንግስት እንደሚገነባ አስታውቀዋል፡፡

የጥፋት ቡድኑ በማይካድራ የፈጸመውን ግፍ የተሞላበት ድርጊት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡድኑ ወደ ህግ እንደሚቀርብም አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ወዳጆች ምስጋና አቅርበው በትግራይ ክልል ከሚገኙ ሲቪል ማህበረሰብ፣ ከህብረተሰቡ ተወካዮች፣ ከሽማግሌዎች እና በክልሉ በህጋዊነት ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እንደሚወያዩም ነው የገለጹት፡፡(FBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top