Connect with us

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡትን ሐሳብ የሪፐብሊካን መሪዎች ውድቅ አደረጉት

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡትን ሐሳብ የሪፐብሊካን ከፍተኛ መሪዎች ውድቅ አደረጉት
Photo: Social Media

አለም አቀፍ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡትን ሐሳብ የሪፐብሊካን መሪዎች ውድቅ አደረጉት

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡትን ሐሳብ የሪፐብሊካን ከፍተኛ መሪዎች ውድቅ አደረጉት

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጪው ኅዳር የሚካሄደውን የ2020 የአሜሪካ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡትን ሐሳብ የሪፐብሊካን ከፍተኛ መሪዎች ውድቅ አድርገውታል።

የላይኛው ምክር ቤት ሴናተር መሪ ሚች ማክኮኔል እና የታችኛው ምክር ቤት መሪ ኬቪን ማክካርቲ ናቸው ሐሳቡን ውድቅ ያደረጉት።

ምርጫው ከኮሮናቫይረስ ጋር በተገናኘ በፖስታ ሊደረግ መታሰቡ ሊጭበረበር ይችላል በሚል ፕሬዚዳንቱ ሐሳብ አቅርበው ነበር።

ሥልጣኑ የኮንግረንሱ እንደሆነ የገለጹት አባላቱ ፕሬዚዳንቱ ምርጫው እንዲራዘም ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል።
የሀገሪቱ መንግሥት ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ምርጫው በፖስታ እንዲደረግ ታስቦ ነበር።

ሆኖም ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዚህ መልኩ የሚደረገው ምርጫ ለመጭበርበር የተጋለጠ እና አስተማማኝ አይደለም በሚል እንዲራዘም ባቀረቡት እቅድ ዙሪያ ከፓርያቸው ሪፐብሊካን አመራሮች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top