Connect with us

ኃይሌ ገብረሥላሴ-ኃይሉን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የሚያድሰው ኢትዮጵያዊ

ኃይሌ ገብረሥላሴ-ኃይሉን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የሚያድሰው ኢትዮጵያዊ
Photo: Facebook

ስፖርት

ኃይሌ ገብረሥላሴ-ኃይሉን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የሚያድሰው ኢትዮጵያዊ

ኃይሌ ገብረሥላሴ-ኃይሉን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የሚያድሰው ኢትዮጵያዊ፤ በኢትዮጵያዊነቴ ብኮራም በኃይሌ ሀገራዊ ፍቅር ግን አብልጬ እቀናለሁ፡፡ | ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የኃይሌ ዓይነት ሰው ነው፡፡ የኃይሌ ዓይነት ሰዎች ዜጎች ማንን መግደል እንዳለባቸው በማቀናጀት ሳይሆን ዜጎች ምን መብላት እንዳለባቸው ተበድሮ በማልማት ይጠመዳሉ፡፡ ኃይሌ ከሜይዳሊያው በኋላ የፈገግታው ምንጭ የፈጠረው የስራ እድል ሆኗል፡፡

በኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ውስጥ በሰራተኛ ጉልበት ሳይሆን በረዥም ዘመን ትርፍ ስሌት በልዩነት የሆቴል ኢንዱስትሪ ዘርፍን የተቀላቀለ አትሌት ነው፡፡ ሀገሩን ቢያስጠራም ዓለም በሩን የሚከፍትለት የትም ሀገሩ መሆን የሚችል ሰው መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ኃይሌ የሀገር ስም ከስሙ ጋር የተሸከመ ኩራት ነው፡፡

ዛሬም ኃይሌ የወገኑ ጉርስ ያሳስበዋል፡፡ ሃይሌ ወገኑን ለማጉረስ ደፋ ቀና ሲል በክፉ መንገድ የሚሄዱ ደግሞ የገዛ ወገናቸው በሃይሌ ጉርሻ ነገን ተስፋ አድርጎ እንዳይኖር ሞሰብ ይገለብጣሉ፡፡

ሻሸመኔና ዝዋይ የኃይሌ ገብረ ስላሴ የሆቴል ኢንቨስትመንት ጌጣቸው ነበር፡፡ ኃይሌ ሪዞርት ከበቀለ ሞላ በኋላ ለሀገር ለማትረፍ የሆቴልን ዘርፍ እያዳረሰ ነገ ከሚያድገው ኢንዱስትሪ ለመጠቀም የገባ ነው፡፡

ኃይሌ የለማ ከተማ መርጦ ሳይሆን ከተማ እንዲለማ ቆርጦ የተነሳ ባለ ራዕይ ነው፡፡ ያ ባይሆን ቅንጡ ሪዞርቶቹ ዛሬ ከቦሌ ጎዳና እስከ ፒያስ ብቻ በተዘረጉ ነበር፡፡

አትሌቱ፣ ሻለቃው፣ ሽማግሌው ተጫዋቹና ሀገር ወዳዱ ኃይሌ ጥቅልል ሲል የኢትዮጵያዊነት ምልክት ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ደግሞ ከፍ ያለ ምልክት፡፡ ትናንት ብቻውን ያሰበው ዛሬ ግዙፍ የስፖርት ቱሪዝም መዲና ባለቤት አድርጎን ከትንሽ ጀምሮ የታላቁ ሩጫ ባለቤቶች አድርጎናል፡፡

በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ የኃይሌን ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ግን እቀናበታለሁ፡፡ ሙሉ ነው፡፡ ሊያጎድሉት ሲቀንሱለት ብዙ እጥፍ የሚሞላ፡፡

የሶስት መቶ ሚሊዮን ንብረት ወድሞበት ንብረቱ ሞሰባቸው ስለነበረ ዜጎች የእለት ጉርስ የሚጨነቅ ስሱ ሰው፡፡ እንዲህ ለወገን በሚተርፍ ልቡ ነገን ጥሩ እንዲሆን የሚያስብ፡፡ እርግጥ ኃይሌ መድረሻ የሌለው ዓልሚ አይደለም፡፡ እንደ ባቱ ሁሉ የኬኒያ ተራሮች የታንዛኒያ ዱሮች የአፍሪካ መዲናዎች ጥሪቱን ቢያገኙ ስመ ጥሩውን አትሌት ስለ ስማቸው አክብረው ይቀበሉታል፡፡

የኃይሌ ገብረ ስላሴ መንፈስ ከሀገሩ የተጣበቀ ሀገሩን እንደ እግሮቹ በራዕዮ ቀዳሚ ሊያደርጋት የሚባትል ቁጭ ብዬ ብበላስ ከሚል ራስ ወዳድነት ተላቆ ዜጋ የሚበላው ቢያገኝስ በሚል ለዜጋ የስራ እድል የሚጨነቅ ነው፡፡ በዚሁ ሁሉ ሀሳቡ ውስጥ ፈተና ሲገጥመው አይወድቅም ይልቁንስ ሀገርን ያጽናናል፡፡ የኃይሌን ቅን መንፈስ ለሀገሬ ሰው ሁሉ ቢሰጥልኝ ስል ተመኘሁ፡፡ ያን ቅን መንፈስ እሻዋለሁና፤

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top