Connect with us

ህወሃት ለስልጣን ካገኘችው ፍልስፍና ጋር የመተኛት ጠባይዋ የዛሬ ወይስ የትናንት?

የርዕዮተ አለም ዘማዊቷ ህወሃት ለስልጣን ካገኘችው ፍልስፍና ጋር የመተኛት ጠባይዋ የዛሬ ወይስ የትናንት?
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ህወሃት ለስልጣን ካገኘችው ፍልስፍና ጋር የመተኛት ጠባይዋ የዛሬ ወይስ የትናንት?

የርዕዮተ አለም ዘማዊቷ ህወሃት ለስልጣን ካገኘችው ፍልስፍና ጋር የመተኛት ጠባይዋ የዛሬ ወይስ የትናንት?
ከስናፍቅሽ አዲስ

ህወሃት ከኦነግ ጋር መፋቀሯ ከርዕዮተ ዓለም ዘማዊነቷ ጋር ይገናኛል፡፡ ትግራይ መስጂድ አላሰራም ብላ ደቡብ ኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ ጠላት ናት ብላ መስበኳ እኮ ብዙ ሚሊዮኖች የሚያውቁት ገበናዋ ነው፡፡

ድህረ መለስ ዜናዊ እንደ ህወሃት ራቁቱን የቀረ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ አልታየም፡፡ አቶ መለስ በመርህ በኩል አይታሙም ሰውዬው ብቻቸውን ቢሆን ይቆማሉ እንጂ ሸምበቆም ቢሆን ልደገፈው አይሉም፡፡

እርግጥ ህወሃትን በርዕዮተ ዓለም ጉዳይ ደጋግመው ምሁራኑ ያሟታል፡፡ የርዕዮተ ዓለም ዘማዊት ናት ሲሉ ላገኘችው ፍልስፍና የምትሴስን መሆኗን ይናገራሉ፡፡ አንዳንዴም ቅጥ አልባ ፍልስፍና በማራመድ ወደር የላትም ለዚህ ማሳያ አብዮትን ከዲሞክራሲ አጣምራ ሀገር እመራለሁ ስትል የባከነችው ነው ይላሉ፡፡

ነገሩ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ግን ብሶበታል፡፡ ጠንካራዎቹ ታጋዮች በራስ መተማመናቸው ጠፍቶ ሸንበቆ ከመደገፍ አልፈው ተጋድመውበታል፡፡ አሌክስ አብረሃም እንዳለው ተራሮችን አንቀጥቅጠናል ያሉት ሱቅ ዘርፎ የወገኑን ቤት ከሚያቃጥለው ወሮ በላ ጉያ ተወሽቀው ቤተ መንግስት ለመግባት ሲያስቡ ታይተዋል፡፡

ህወሃት አሁን ለስልጣን ስትል ከየፍልስፍናው የምትጋደም ዘማዊ ሆናለች፡፡ ፍልስፍናዋ አይጣረዝባትም ለምሳሌ እኔ ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ለውጥ አምጥቻለሁ ትልና የለም ጨፍጫፊ ነበርሽ ብሎ የሚጸየፋትን እንደ ሀጫሉ ያለ ታጋይ የህዝብ ልጅ ብላ በሚዲያ ጀግንነቱን ትሰብካለች፡፡ እንዲህ ስትሆን ልኩ የቱ ጋር እንዳለ ሰሚን እንኳን እንደሚቸግረው ማሰብ ያቅታታል፡፡

ሰሞኑን በመላው ዓለም ከኦነግ ጋር በጋራ በመቆም ዶክተር አብይንና የብልጽግናውን ሃይል ለመጣል ሁለትም ሶስትም ከሆኑ ሰልፈኞች ጋር ባንዲራ ይዛ ብቅ ብላለች፡፡ በእርግጥ እንዲህ ባንዲራ ይዛ ለመቃወም እስክትበቃ ያደረሷት ዛሬ አብራቸው ሰልፍ የወጣችው ቢሆኑም እሷ ፍልስፍና አልባ ፓርቲ ሆናለችና አይገዳትም፡፡ የቆመችበትን ማየት አትፈልግም ወደ አራት ኪሎ የሚወስድ መንገድ ከመሰላት ከማንም መርህ ጋር አብራ ለመተኛት የማትጸየፍ የጎዳና ተጓዥ ናት፡፡

የትናንትናዋ ህወሃት እንዲህ ናት የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም ህይወቱ ያለፈው መሪዋ ግን ብቻውን ለመቆም ፍራት የማይሰማው ማዕከላዊውን ጠርጎ አዲስ ፓርቲ በመስራት አዲስ መንገድ ለመጀመር ያላመነታ ነበር፡፡ ያኔ በድብቅ እንዲህ ያለ ጠባይ ቢኖራትም ዛሬ ግን የአደባባይ ገበናዋ ሆኗል፡፡ አብን ነይ ሰልፍ እንውጣ ቢላት አብንዬ ለማለት የማይገዳት፣ ብልጽግና ቢያሽኮረምማት ለመሳቅ የማትሳቀቅ፣ ሌላው ቀርቶ ጓድ ሊቀመንበር አብይን እንጣል ቢሏት መቀሌ ፎቷቸውን ሰቅላ ታላቁ መሪ ለማለት የማትሸማቀቅ ጉድ ናት፡፡ እሷ በዚህ ወቅት ቅዠቷ ስልጣንና ገንዘብ ነው፤ ያ ካለ የስድሳ ሺህ ህዝብ የህይወት መስዋዕትነት በእሷ ዘንድ ዘፈንና ዘጋቢ ፊልም እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top