Connect with us

ልደቱ አያሌው ታሰሩ

ልደቱን ፖሊስ አለቅም ማለቱ ተሰማ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ልደቱ አያሌው ታሰሩ

የቀድሞ የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ፖሊስ መታሰራቸውን የወቅቱ የኢዴፓ ኘረዝደንት አቶ አዳነ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው አረጋግጠዋል።

አቶ ልደቱ የፍርድ ቤት መጥሪያ በያዙና በኦሮሚያ ፖሊስ በአዲስአበባ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የታሰሩበት ምክንያት ቢሾፍቱ ከተማ ላይ የተቀሰቀሰውን ቀውስ አስተባብረሃል፣ በገንዘብ ደግፈሃል በሚል በመጠርጠራቸው ነው ተብሏል።

አቶ ልደቱ በቅርብ ከእነጀዋር መሐመድ ጋር የሚናበብ በሚመስል መልክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚያራምዱት የከረረ ፓለቲካ በቀድሞ የትግል አጋሮቻቸው ጭምር ግልፅ ተቃውሞን እንዳስከተለባቸው የሚታወቅ ነው።

ከአቶ ልደቱ ጋር አብረው አብሮነት በሚል ጥምረት መስርተው ከሚንቀሳቀሱት መካከል ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በተመሳሳይ ሁኔታ በቅርቡ መታሰራቸው የሚታወስ ነው።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top