Connect with us

በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ የተጠረጠሩ ቃል መቀበል ተጠናቀቀ

በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ የተጠረጠሩ ቃል መቀበል ተጠናቀቀ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ የተጠረጠሩ ቃል መቀበል ተጠናቀቀ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰኔ 15 የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ የተጠረጠሩ ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ተቀብሎ በማጠናቀቁ ማን ለማን ያስረዳል የሚለውን ዝርዝር በቁጥር እንዲያቀርብ ለዐቃቢ ህግ ትዕዛዝ በመስጠት ለሃምሌ 24 ቀጠሮ ሰጠ፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ የተጠረጠሩት በነ ሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ የተከሰሱ 49 በማረሚያ ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ከዚህ በፊት ተጠርጣሪዎቹ ያቀረቡትን የክስ መቃዎሚያ ውድቅ ያደረገው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን መፈጸም አለመፈጸማቸውን የዕምነት ክህደት ቃል በመቀበል ዛሬ አጠናቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በኮሮና ምክኒያት በከፊል ስራ እንዲሰራ በወሰነው መሰረት 49 ተከሳሾችን በአንድ አድርጎ ጉዳያቸውን ማየት የኮሮና በሽታን በማስፋፋት የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በመረዳት እና ጉዳዩ ደግሞ መታየት አለበት የሚል ውሳኔ ላይ በመድረሱ በአንድ ጊዜ 6 ተከሳሾችን ችሎት እንዲቀርቡ በማድረግ የ49 ተከሳሾችን የዕምነት ክህደት ቃል የተቀበለ ሲሆን ሁሉም ተከሳሾች ድርጊቱን አልፈጸምንም በሚል ክደው ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪዎችን ድርጊቱን አልፈጸምንም በሚል ክዶ መከራከር መሰረት በማድረግ ዐቃቢ ህግ ያቀረባቸው 167 የዐቃቢ ህግ ምስክሮች ወደ መስማት የሚሄድ በመሆኑ ሁሉንም ምስክሮች በአንድ ጊዜ ለመስማት ከኮሮና አንጻር ስለማይቻል የትኛው ምስክር ማን ለማን ያስረዳል የሚለውን ለይቶ እንዲያመጣ ፍርድ ቤቱ ለዐቃቤ ህግ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ዐቃቢ ህግ ፍርድ ቤቱ ባዘዘው መሰረት ባለማምጣቱ ማን ለማን ያስረዳል የሚለውን ዝርዝር በቁጥር እንዲያቀርብ ለዐቃቢ ህግ ትዕዛዝ በመስጠት ችሎቱ ለሃምሌ 24 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡(የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top