Connect with us

“በዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ላይ አምባገነናዊ መፍትሔ ውጤት አያመጣም”

“በዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ላይ አምባገነናዊ መፍትሔ ውጤት አያመጣም”- በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር
Photo: EPA

አለም አቀፍ

“በዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ላይ አምባገነናዊ መፍትሔ ውጤት አያመጣም”

በዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ላይ አምባገነናዊ መፍትሔ ሳይሆን የሦስቱ አገራት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ድርድር ውጤት እንደሚያመጣ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጄኒይ ተረክህን ገለፁ።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጄኒይ ተረክህን የዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የዓባይን ወንዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀም በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሩሲያ ከሦስቱም አገራት ጋር በወዳጅነት እና ቅርበት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዳላት ያነሱት አምባሳደሩ፣ ግንኙነቱ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ መሆኑን አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት በሦስቱ አገራት መካከል የተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት ሩሲያን እንደሚያሳስባት እና ጉዳዩን በትኩረት እየተመለከተችው መሆኑንም ተናግረዋል።

“በዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ዙሪያ የሚደረገው የሦስትዮሽ ድርድር የሦስቱንም አገራት ኤኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ብሔራዊ የጥቅም ፍላጎት በማያጓድል መልኩ መፍትሔ የሚሰጥ መሆን አለበት” ብለዋል።

በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በግድቡ ዙሪያ የሦስቱን አገራት መሪዎች አቀራርቦ በማወያየት ድጋፍ እና እገዛ ማድረጉን አምባሳደሩ አስታውሰዋል።

በእዚህም ህብረቱ አገራቱን በማስማማት በኩል ከፍተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

“ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” በሚባለው መርህ መሠረት አገራቱ ከተግባቡ ጥሩ ውጤት ላይ መድረስ እንደሚቻል አምባሳደር ኢቭጄኒይ ተናግረዋል።

አገራቱ የሚያደርጉትን ድርድር ከውጤት ማድረስ የሚቻለው ደግሞ አምባገነናዊ መፍትሔ በመውሰድ ሳይሆን ፣ለሦስቱም አገሮች ፍላጎት ተስማሚ የሆነ ውጤት ላይ እንዲደረስ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ሲወያዩ ብቻ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሥራ 74 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top