Connect with us

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኦሮሞ ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኦሮሞ ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት
Photo: Facebook

ዜና

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኦሮሞ ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት

የኦሮሞ ህዝብ አንድነቱን አጠናክሮ ወደ ቀድሞው የማንነቱ እሴቶች መመለስ አለበት – ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ

የኦሮሞ ህዝብ ቀድሞ የሚታወቅባቸውን እንደ ጉዲፈቻ፣ አቃፊነት እና ሰውን ወዳድነት እንዲሁም ባዳን ዘመድ የማድረግ እሴቶቹን ይበልጥ በማጠናከር የተጀመረውን ለውጥ ለማሻገር በግንባር ቀደምትነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ባለፉት ስርዓቶች የኦሮሞ ህዝብ ጥላቻ እና መገፋት ደርሶበታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ይህን መገፋትና ማግለል በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ላይ ለመድገም ማሰብ አይገባም ብለዋል ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፡፡

ሁሉም ከውሸት ፣ ከቅናትና ከሌብነት በመውጣት ህዝቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚጠበቅበት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሳስበዋል።

የኦሮሞ ህዝብ የቀድሞ የማንነቱ እሴቶችን ተግባራዊ በማድረግ ከሌሎች ብሄር ብሔረሰቦች ጋር በፍቅር ፣ በአንድነት እና በመተባበር መቆም ከቻለ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን የማድረጉ ጉዞ እሩቅ አይሆንም ማለታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል:: #ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top