Connect with us

የኢዜማ አባሏ ታሰሩ

የኢዜማ አባሏ ታሰሩ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

የኢዜማ አባሏ ታሰሩ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ·ም ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ በፖሊስ ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው መታሰራቸውን ፓርቲው ገለፀ።

ከትላንት በስቲያ ከሰዓት ፖሊስ መኖሪያ ቤታቸውን የፈተሸ ሲሆን 3 የተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎዎችን፣ አንድ ልጃቸው የሚገለገልበት ከሚሠራበት ድርጅት የተሰጠው ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና አንድ የቤተሰብ ዝግጅት የተቀዳበት የቪዲዮ ካሴት ከቤታቸው ወስዷል።

ሂሩት ተይዘው በሚገኙበት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተጠርጣሪዎች ማቆያ ከጠበቃቸው (የኢዜማ ጠበቃ) ጋር ትላንት ሐምሌ 8 ቀን 2012 ዓ·ም ከሰዓት ተገናኝተው ስለተያዙበት ሁኔታ ተወያይተዋል። ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top