Connect with us

አቶ በረከት ስምዖን ካሉበት ኮሚኒኬሽኑን ቢመሩትስ?

አቶ በረከት ስምዖን ካሉበት ኮሚኒኬሽኑን ቢመሩትስ?
Photo: Social Media

ፓለቲካ

አቶ በረከት ስምዖን ካሉበት ኮሚኒኬሽኑን ቢመሩትስ?

ኮሚኒኬሽን ተቋም የሌላቸው ጠቅላይ ሚኒስትርና ስለራሳችን ዓለም የሚነግረን እኛ ኢትዮጵያውያን፡፡
አቶ በረከት ስምዖን ካሉበት ኮሚኒኬሽኑን ቢመሩትስ?
አስቸኳይ መግለጫ የሚዘገይባት ሀገር፡፡
******
ከስናፍቅሽ አዲስ

የዓለም መገናኛ ብዙሃን የግድቡን ሙሌት አስመልክቶ የተለያዩ ዘገባዎችን ሲለቁ አድረዋል፡፡ በተቃራኒው የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሃላፊዎችና ሚዲያዎች ደግሞ የሞት ያህል ድብን ባለ እንቅልፍ አንግተዋል፡፡ ሲነሱ የሆነው ግን ሌላ ነው፡፡ ዜጎች ከውጪ በሰሙት መረጃ ተረብሸው ተጨንቀውና እውነት ይሆን እያሉ ተሰቃይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተሳካላቸው የኮሚኒኬሽን ዘርፉ ይመስለኛል፡፡ ጥናት ቢፈልግም እንኳን በደምሳሳው ለታዘበ ግን ጠቅላዩን ከሰው ያራቃቸው ያቀራርበኛል ያሉት የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ነው፡፡ ሀሰተኛ መረጃዎች፣ ያልተፈጸሙ ቃላት፣ የተወናበዱ መግለጫዎች የለውጥ ሃይሉ የተግባቦት ተግባር የስራ ሃላፊዎች መለያ ተግባር ሆኖ ከርሟል፡፡

ግብጾች ውይይቱ እንዳለቀ ዓለምን ያዳረሰ መረጃ ለቀቁ ያ መረጃ ሲለቀቅ ግን ባላንጣችን ያሏት ሀገር እንደሞላላት ባልቴት ጥሩ እንቅልፍ ተኝታ ወፍ እስኪጮህ ትጠብቅ ነበር፡፡ ግብጻውያን ሃላፊነት የሰጡት መንግስት በአባይ ጉዳይ ምን እንደደረሰ ሰረስኩበት ያለውን ሲነግራቸው፡፡ ያ መረጃ እውነት ይሁን ውሸት ግን በእኛ በኩል መረጃ የነገረን ማንም የለም፡፡ ሲነጋም ቀን መረጣ የገባው የመንግስት መግለጫ ምቹ ሰዓት እስኪያገኝ ሀገሩን የውጪው ሚዲያ መረጃ ነገሰበት፡፡

ቀደም ባለው የመንግስት መዋቅር ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የተዋጣለት እንደነበር በወቅቱም ሆነ ዛሬ ደጋግሞ ሲወደስ ይደመጣል፡፡ አቶ በረከት ስምዖን የኮሙኒኬሽን እና የፕሮፖጋንዳ ስራው ላይ የነበራቸው ብቃት ግድቡ መሰረቱ ሲጣል ባሳዩት ብቃት ታይቷል፡፡ ያኔ ዜጎች በመረጃ አልተወናበዱም፡፡ እንዲህ ባለው ወቅት አቶ በረከት ስምዖን ካሉበት ሆነው ዘርፉን በመሩት ያስብለናል፡፡ አሁን ኢትዮጵያውያንን ስለራሳችን ቀድሞ የሚነግረን የሌላው ዓለም ሚዲያ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ አስቸኳይ መግለጫ ይዘገያልና፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top