Connect with us

“አብይን አላምነውም” የቀድሞ አምባሳደር ሥዩም መስፍን

"አብይን አላምነውም" የቀድሞ አምባሳደር ሥዩም መስፍን
Photo: Social Media

ፓለቲካ

“አብይን አላምነውም” የቀድሞ አምባሳደር ሥዩም መስፍን

“አብይ አህመድ በ ፕረዚደንት ትረምኘ እና አልሲሲ ያለውን ስምምነት ረግጦ መሄድ አይችልም። ግብፅ 37 ቢልዮን ኲሜ ውሃ በአመት እንድትወስድ አብይ አህመድ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ትረምኘ ትንሽ ነው የጨመረው።

“በናይል ጉዳይ በኢህአዴግ አመራር ዘመን ታሪክ መቀየር የቻለ አኩሪ ስራ ነበረ የተሰራው፡፡ አስሩ የአባይ ተፋሰስ አገሮች ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈው ግብፅን ሞግተዋል፡፡ በአባይ ጉዳይ ኢትዮጵያ ትምራን እስከማለትም ደርሰው ነበረ፡፡

አብይ አህመድ እነዚህ ከኢትዮጵያ ጥቅም ጎን ተሰልፈው ሲሰሩ የነበሩ አገሮችን ወደ ጎን በመተው እኮ ነው ወደ አሜሪካ የሄደው፡፡ እየሄድኩ ነውም አላላቸውም፡፡ ግብፅን ይዞ ነው ወደ ዋሺንግተን የሄደው፡፡ ሱዳንም በኃላ ነው ወደ አሜሪካ የተጠራችው እንጂ አብይ አልነገራቸውም፡፡

አብይ ከመጀምሪያው ጀምሮ የህዳሴ ግድብ ለፖለቲካ ፍጆታ የተጀመረ ነው ብሎታል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ከተጠረጠረ በኋላ ነው እየዘመረለት ያለው፡፡ ለድርድር ሲለኩ የቆዩ የግድቡ ሞያተኞች ናቸው፤ ተው! እየተሳሳትክ ነው ያለኸው፤ የውጫሌ ሁለተኛ ስህተት እየተሰራ ነው፤ ማቆም አለብህ ብለውታል፡፡

አብይ አህመድ ነገ ጠዋት በክህደት (treason) የሚያስጠይቅ ክህደት ነው የፈፀመው፡፡ በፓርላማ ቀርቦ የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ እርዳታ የእናት እርዳታ ነው ብሏል፡፡ በአሁኑ ሰአት እነዚህ ጌቶቹ ምን እያሉት እንደሆነ እንመልከት፡፡ ከግብፅና ሱዳን ሳትስማማ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት የምትጀምር ከሆነ ለማካካሻ ቃል የተገባልህ ገንዘብ አንሰጥህም ብለዋል፤ በግላጭ፡፡

በአገራችን ውስጥ የትረምኘ እና ዩክሬን ታሪክ እኮ ነው እየተደገመ ያለው፡፡ በትረምኘ እና አልሲሲ ያለው ስምምነት፣ በአድርግልኝ ላድርግልህ የተመሰረተ ነው፡፡ አብይ፣ ይህን ስራ እንዳይሰራ ከልክልልኝ፤ እኔ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ላለህ ፍለጎት አስፈፅምልሀለሁ፤ ተባብለው ነው እየሄዱ ያሉት፡፡

አብይ ይህንን ረግጦ መሄድ አይችልም፡፡ በመሃል ተንጠልጥሎ ለመሄድ የሚያስችል እድልም የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እያለው እንዳለም በግልፅ እየተመለከተ ነው፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ፖሊሲ ደግሞ አንዴ እዛ ሄዶ ሸጦታል፡፡ በህዳሴው ግድብ ከኛ ጋር ቆመው ሲያግዙን የነበሩ አስር አገራትም አንዴ እነሱን ትቶ ስለሄደ ለብቻው ነው ወዲያ ወዲህ እያለ ያለው፡፡

ያም ሆነ ይህ እኔ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ እኔ አብይን አላምነውም፡፡ ይህንን ግድብ ምናልባት ሊፈርስ የሚችል ከሆነ፣ አሰራሩ ፅኑ ነው፤ ወይስ አይደለም? ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ብቻ ካልሆነ እያንዳንዱ ሃገር ስንት ቢልዮን ኲሜ ውሃ ይድርሳታል? ለሚለው የናይል ቤዚን ኮሚሽን ከተቋቋመ በኃላ ነው የምናየው ነው፡፡ አሁን ወደዚህ አንገባም ብለናል እኮ፡፡

ይህን በሆነበት ሁኔታ ግብፅ 37 ቢልዮን ኪሜ ውሃ በአመት እንድትወስድ አብይ አህመድ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ትረምኘ እኮ ትንሽ ነው የጨመረው፡፡

የውሃ ሙሊትም ቢሆን ውሃ ሞምላት ጀምረናል ሊለን እኮ ይችላል፡፡ ግን የሚሞላው የውሃው መጠን ስንት እንደሆነ ማን ነው የሚለካው? በዚህ ክረምት የሚሞላው ውሃ ስንት እንደሆነ ማን ነው ለክቶ የሚነግረን፡፡

አብይ አህድ በሚሄደው መንገድ ማን ሊያምነው ይችላል? እንዴት አድርገህ ማመን ይቻላል? እኔ አላምነውም፡፡ ምክንያቱ አብይ እንዴት አድርጎ ስልጣን ላይ እንደሚቆይ ብቻ ነው የሚያስበው፡፡ ግድቡ ደግሞ አንዴ ሸጦታል፡፡ በዚሁ ተግባር ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡”

( ምንጭ:-BBC Tigrinya፣ ህወሓት ድረገፅ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top