Connect with us

የጠገበ ጅብ ሸኝተን የራበው እያነገስን እንዳይሆን!

የጠገበ ጅብ ሸኝተን የራበው እያነገስን እንዳይሆን !
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የጠገበ ጅብ ሸኝተን የራበው እያነገስን እንዳይሆን!

የጠገበ ጅብ ሸኝተን የራበው እያነገስን እንዳይሆን! | በሳምሶን ሚካሄሎቪች

ከወደ አዲስአበባ የሚነሳው የህዝብ ቅሬታ እንዲሁ ችላ ብለው የሚያልፉት አይደለም። የቀድሞ ገዥዎቻችን ለነገ ብለው ያሳደሩትን መሬትና የቁጠባ ቤት አዲሶቹ ሹመኞቻችን ለከስአትም ማዋል አቅቷቸው እንደ ቅርጫ እየተከፋፈሉት እንደሆነ ነዋሪው ወረዳና ቀበሌ ጠቅሶ ” የህግ ያለህ ! ” እያለ ነው።

የመሬት ቅርምቱ ሳይበቃ ህዝብ እናገለግላለን ያሉ ሹመኞች መጀመሪያ አይናቸው የሚያርፈው የከተማው ህዝብ ቆጥቦ የገነባቸው ኮንዲምኒየም ህንጻዎች ላይ ነው። በግሌ አንድም ሹመኛ ከተራው ህዝብ ለቁጠባ መኖሪያ ቤቶች ቅድሚያ ማግኘት የለበትም።

ከጉዳዩ ጋር ባይገናኝም ለምሳሌ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ ከ £ 5 የበለጠ ስጦታ የተቀበለ የማንግስት ሰራተኛ በቀጥታ ከስራው ይባረራል። እንኳንስ በስራው ምክንያት የመንግስት ቤትና መኪና ለማግኘት።

ሹመኞች ከግብር ከፋዩ ህዝብ በተሰበሰበ ገንዘብ የተገዙ ቅንጡ መኪናዎች ሲያሽከረክሩና ሽንኩርትና በርበሬ ሲገዙባቸው ዝም ያለ ህዝብ ዛሬ ቆጥቦ የሰራው መኖሪያ ቤት ለእነርሱው እጅ መንሻ እየሆነ ነው።

የዶ/ር አቢይ መንግስት ስልጣን ሲይዝ ለህዝብ ቃል ገብቶ ላለፈው ህጸጽ ይቅርታ ጠይቆ ነው። ህዝብ አዲስ ጅቦች በየቀኑ ማየት ሲጀምር ዳግም ” አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ ? ” እያለ ማዜሙ አይቀርም።

የአቢይ አስተዳደር በጎ ሲሰራ አበጃችሁ እንዳልን ሁሉ ደሀው ኢትዮጵያዊ ላይ አዲስ ጅብ ሲለቅበት ዝም ማለት የጅብ ተላላኪ ከመሆን ያለፈ ሚና የለውም።

የመንግስት ሹመት ህዝብ ለማገልገል የሚከፈል መስዋዕት እንጂ የግል ጥቅም ማካበቻ መሆኑ ማብቃት አለበት። አንድም ሹም ፣ እደግመዋለሁ አንድም ሹም በስልጣኑ ሳቢያ ከህዝብ ቀድሞ የተሻለ ጥቅም ሊያገኝ አይገባም ! ይሄ ሌብነት ነው !!!

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top