Connect with us

ሶስቱ አገራት ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ

ሶስቱ አገራት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ
Photo: Social Media

አለም አቀፍ

ሶስቱ አገራት ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ

ሶስቱ አገራት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ሰለማዊ በሆነ መንገድ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳስቧል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፋን ጃሪክ እንደተናገሩት ሀገራቱ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በልዩነቶቻቸው ላይ በጋራ መምከር ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ሲጂቲ ኤን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።

ቃል አቃባዩ ሀገራቱ እ.ኤ.አ. በ2015 በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነቶች ዓለም አቀፍ ህጎችን መሰረት በማድረግና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ ሁኔታ በትብብር መንፈስ ለመፍታት ያስቀመጡትን መርህ በመከተል ለችግሮቻቸው እልባት ማበጀት እንደሚገባቸውም ነው የገለፁት።

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top