Connect with us

ፑቲን ለተጨማሪ 12 አመታት በሥልጣን ለመቆየት እንደሚሹ ጥቆማ ሰጡ

ፑቲን ለተጨማሪ 12 አመታት በሥልጣን ለመቆየት እንደሚሹ ጥቆማ ሰጡ
© Alexei Nikolsky/Russian Presidential Press and Information Office/TASS

አለም አቀፍ

ፑቲን ለተጨማሪ 12 አመታት በሥልጣን ለመቆየት እንደሚሹ ጥቆማ ሰጡ

የሩሲያ ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያ ከጸደቀ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለተጨማሪ አመታት በሥልጣን ለመቆየት እንደሚፈልጉ ተናገሩ።

ሩሲያውያን ከመጪው ሰኔ 18 እስከ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል በቀረው ሐሳብ ላይ ድምፅ ይሰጣሉ። በማሻሻያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለተጨማሪ 12 አመታት በሥልጣን እንዲቆዩ የሚፈቅድ አንቀጽ ተካቶበታል። የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሥልጣን ከአራት አመታት በኋላ ይጠናቀቃል።

ተቃዋሚዎች የሕገ-መንግሥት ማሻሻያው ፑቲንን እስከ ጎርጎሮሳዊው 2036 ዓ.ም. በሥልጣን ለማቆየት የታቀደ “ሕገ-መንግሥታዊ መፈንቅለ መንግሥት” ነው ሲሉ ይከሳሉ። የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ማሻሻያው የምክር ቤቱን ሚና፣ ማኅበራዊ ፖሊሲ እና የሕዝብ አስተዳደርን ለማጠናከር የታቀደ ነው ብሏል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዛሬው ዕለት ለአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌብዥን “በሕገ-መንግሥቱ ከቀረበ ለሥልጣን ድጋሚ ለሥልጣን ልወዳደር እችላለሁ” ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ “ገና አልወሰንኩም” ሲሉ ተናግረዋል።

በሩሲያ ምክር ቤት እና ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ቀድሞም የጸደቀው ማሻሻያ ፕሬዝዳንት ፑቲን እስካሁን በሥልጣን የቆዩባቸውን አመታት ሰርዞ እንደገና ከዜሮ እንዲጀምሩ ዕድል ይሰጣቸዋል። አሁና ባለው ሕገ-መንግሥት ፑቲን በድጋሚ ለፕሬዝዳንነት መወዳደር አይችሉም።

ለሁለት አስርት አመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት የ67 አመቱ ፑቲን በድጋሚ ካልተወዳደሩ ተተኪ እጩ ፍለጋው ዕክል ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ዛሬ ከብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ጥቆማ ሰጥተዋል። DW

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top