Connect with us

ዚ ቲቪ ከዲኤስቲቪ ጋር በመተባበር በአማርኛ የተዘጋጀ አዲስ ቻናል ሊጀምር ነው

ዚ ቲቪ ከዲኤስቲቪ ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ በአማርኛ የተዘጋጀ ዚ አለም የተሰኘ አጓጊ አዲስ ቻናል ሊጀምር ነው!
Photo: Social Media

መዝናኛ

ዚ ቲቪ ከዲኤስቲቪ ጋር በመተባበር በአማርኛ የተዘጋጀ አዲስ ቻናል ሊጀምር ነው

በመላው ህንድ የቴሌቪዥን፡ የሚዲያና የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ ከሚመሩት ግዙፍ ተቋማት አንዱ የሆነው ዚ ኢንተርቴይንመት ኢንተርፕራይዝ ሊሚትድ ዚ አለም የተሰኘ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች በአማርኛ የተዘጋጀ አዲስና ልዩ ቻናል ሊጀምር መሆኑን ይፋ አድርጓል! አዲሱንና እጅግ አዝናኝ የሆነውን በአማርኛ የተዘጋጀውን ዚ አለምን የዲኤስቲቪ ደንበኞች ከሰኔ 15፣ 2012 ጀምሮ ዲኤስቲቪ ቻናል 145 ላይ በፕሪሚየም፡ ኮምፓክት ፕላስ፡ ኮምፓክትና ፋሚሊ ፓኬጆች ላይ መመልከት ይችላሉ። ዚ አለም ቻናል ለኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያውን የቦሊውድ አጫጭር ልብወለዶች ይዞ የቀረበ ቻናል ነው።

ዚ ከሁለት አስርተ አመታት በላይ በዲኤስቲቪ ላይ በሂንዲ ቋንቋ የሚተላለፉ የዚ ቲቪ ፕሮግራሞች ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን ፡ ባለፉት 5 አመታት ውስጥ ደግሞ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚተላለፈውን አንጋፋውን ዚ ዎርልድን ጨምሮ በአፍሪካ ውስጥ በዲኤስቲቪ ብቻ የሚተላለፉ በርካታ ቻናሎችን ከፍቷል። ዚ ዎርልድ በአይነቱ የመጀመሪያ ቻናል ሲሆን ፡ በአህጉሪቱ ዋና ዋና የመገናኛ ብዙሃን ቻናሎችን ለሚከታተሉ ተመልካቾች እንዲስማማ ሆኖም ተቀርጿል። የዚ ዎርልድ ስኬታማነት የዚ ሾዎችን ተፈላጊነት በመጨመር በአፍሪካ እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ የቤተሰብ መዝናኛ ቻናሎች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል።

በአለም ዙሪያ ከ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ ተመልካቾችን በ173 አገራት ውስጥ በ46 የህንድና 40 አለማቀፍ ቻናሎች በማዝናናት የሚታወቀውአንጋፋው ዚ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካን ገበያ የተቀላቀለው ከ24 አመታት በፊት ነበር። ከቻናሎቹ ሁሉ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ዚ ቲቪ በአፍሪካዊው ዲኤስቲቪ ላይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1996 ጀምሮ ሲተላለፍ ቆይቷል።

ዚ አለም ከዛሬ ሰኔ 15፣2012 ጀምሮ ተወዳጅና ልብ የሚሰቅሉ ዝግጅቶቹን ማቅራብ ይጀምራል። እነዚህ ተከታታይ ዝግጅቶች ተወዳጆቹን The Promise ( ቃልኪዳን)፡ Lies of The Heart (ልባዊ ውሸቶች) ፡ Married Again ( ፍቅር እንደገና) ፡ Ring of Fire (የእሳት ቀለበት) እናም ሌሎች ተከታታይ ጥንቅሮችን ያካትታል።

በአፍሪካ ብቻ 8 ቻናሎችን በመክፈት ፡ ዚ በቦሊውድ መዝናኛ ኢንደስትሪ ውስጥ አሉ የተባሉትን ስራዎችን ሁሉ ይዞ ቀርቧል!

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top