Connect with us

የሽማግሌዎቹ ድካም ምን ሊያመጣ ነው?

የሽማግሌዎቹ ድካም ምን ሊያመጣ ነው?

ባህልና ታሪክ

የሽማግሌዎቹ ድካም ምን ሊያመጣ ነው?

ህወሃት መብቴ ከተከበረ ጠብ የለኝም ካለች፤ ማዕከላዊ መንግስቱ ምርጫ አይታሰብም ብሎ ከወሰነ፤ የሽማግሌዎቹ ድካም ምን ሊያመጣ ነው?
******
ከስናፍቅሽ አዲስ
ሀገር አቀፍ የሽማግሌዎች ፍላጎት ሀገር ሰላም እንዲሆን ነው፡፡ የሰላም ቁልፉ ማን እጅ ነው ያለው የሚለው? እንደ ህዝቡ ሁሉ ለሽማግሌዎችም እንቆቅልሽ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ቁልፉን ፍለጋ ሲደክሙ ቁልፉ የሌለበትን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ የነበሩት ሁለት ፓርቲዎች እሰጥ አገባ እንዲህ ቀጥሎ ስለሚሆነው አልተነበይ ያለበት ወቅት የለም፡፡ የትግራይ ክልል የምርጫ ማካሄድ ፍላጎቱን ከፓርቲና ከክልሉ መንግስት አስበልጦ የህዝብ ጥያቄ አድርጎታል፡፡

ዶክተር አብይን የሚደግፉ የትግራይ ሰዎች ጭምር ምርጫው ጋር ሲደርሱ አታደርጉም የምትለዋ እግድ ከማንም ብትመጣ ተቀባይነት እንደሌላት አስረግጠዋል፡፡ የአቶ ስዬ አብረሃና የጄነራል ሳሞራ ዬኑስ ንግግር ይሄንን ያስረዳል፡፡

ብልጽግናና ህወሃት እርስ በእርስ በቅጡ ይተዋወቃሉ፡፡ ለዝምድናው ቢሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ የበለጠ እነሱ ዘመዳሞች ናቸው፡፡ እልህ የተጋቡበት ጉዳይ ግራ ያጋባቸው ሽማግሌዎች ለሀገር ሰላም ሲሉ ሽምግልና መርጠዋል፡፡

ጥያቄው ለሽምግልና የሚጠየቀውና “አንተም ተው” “አንተም ተው” የሚባለው ምኑ ነው? ፌዴራል መንግስቱ ትግራይ ምርጫ ታድርግ ብሎ ይስማማል? የትግራይ ክልልስ እሺ ምርጫው ይቅርብኝ ሊል ይችላል? ቀዳሚውና ቁልፉ የልዩነት መንገድ ይሄ ይመስለኛል፡፡

ህወሃት ብቻዬን የምታረቀው ጠላት የለኝም፤ ገዢው ቡድን ከፌዴራሊስት ሀይሎች ጋር የተጣለ ስለሆነ አንድ ላይ ነው ውይይቱ ብላለች፡፡ ብልጽግና ለሀገር ሰላም ሲባል የሽማግሌዎቹን ሙከራ አከበርኩ እንጂ ሽማግሌ አልላኩም የሚል መንፈስ ያለው ሀሳብ በከፍተኛ አመራሮቿ በኩል እየተነፈሰች ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ዳር ቆሞ ቢመለከታቸው መግቢያ የሌላቸው ሁለት የቀድሞ አንድ ፓርቲዎች ትከሻ ለመለካካታቸው ቅራኔ መቶ ሚሊዮን ህዝብ ጦስ ውስጥ ለመክተት አፋፍ ላይ ናቸው፡፡ አፋፉ ላይ ያለው ወገን እንደ በሬው ገደሉን አላየም፤ ሳሩን እንደድጋፍ አሻግሮ እየተመለከተ ሁለት ጎራ ሆኗል፡፡

Continue Reading
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top