Connect with us

ህይወት ይታደጋል የተባለውን መድኃኒት የዓለም ጤና ድርጅት ተቀበለው

ዴክሳሜታሶን የዓለም ጤና ድርጅት ተቀበለው!
Photo: Social Media

ጤና

ህይወት ይታደጋል የተባለውን መድኃኒት የዓለም ጤና ድርጅት ተቀበለው

የኮሮናቫይረስ ጽኑ ህሙማንን ህይወት ይታደጋል የተባለውን መድኃኒት የዓለም ጤና ድርጅት ተቀበለው

በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) በተባለው መድኃኒት ላይ የተደረገው ሙከራና ያስገኘውን ውጤት በበጎ እንደሚመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ከታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል።

ድርጅቱ እንዳለው የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባለቸው ላይ እንዳልሆነ አመልክቷል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት “ይህ ኦክስጂንና የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ላይ የሚያጋጥምን ሞት የሚቀንስ የመጀመሪያው መድኃኒት ነው” ብለዋል።

#BBC

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top