Connect with us

ኮረናን የማሸነፍ ዘዴው ጭንቀትና ፍርሃት ሳይሆን ጸሎትና ጥንቃቄ ነው!!

ኮረናን የማሸነፍ ዘዴው ጭንቀትና ፍርሃት ሳይሆን ጸሎትና ጥንቃቄ ነው!!

ባህልና ታሪክ

ኮረናን የማሸነፍ ዘዴው ጭንቀትና ፍርሃት ሳይሆን ጸሎትና ጥንቃቄ ነው!!

ኮረናን የማሸነፍ ዘዴው ጭንቀትና ፍርሃት ሳይሆን ጸሎትና ጥንቃቄ ነው!!
(ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፤ የሩቅ ምሥራቅ ሀገራት ሊቀ ጳጳስ እና የዓለም የሰላም አምባሳደር)

‘‘አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤’’ (ኢሳ. ፵፣፩)

የኮረና ቫይረስ በዓለማችን ላይ ከተከሰተ ጀምሮ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ጭምር እያሻቀበ ነው፡፡ በአኅጉራችን አፍሪካና በሀገራችን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ ሁናቴ ወርርሽኙ ከባድ የጤና፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ተግዳሮት እየሆነብን ነው፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት ቫይረሱን በተመለከተ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃንና በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች የሚሰራጩ የተዛቡ መረጃዎችም ለብዙዎች የጭንቅትና የፍርሃት ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ ባለፈው ሰሞንም በሀገራችን የኮረና ቫይረስ ይዞኛል በሚል ጥርጣሬ ራሷን በሻሿ አንቃ ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገችው ኢትዮጵያዊ ወገናችን አንድ ማሳያ ናት፡፡

ይህን በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት ሀገራችን የገባችበትን አስጨናቂ ጊዜ መሠረት በማድረግ፣ በአርባ ምንጭ የኮረና ቫይረስ ይዞኛል በሚል ጥርጣሬ ራሷን በሻሿ አንቃ ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገችውን ኢትዮጵያዊ እህታችንና እንዲሁም በአስገድዶ መድፈር ምክንያት ትካዜና ኃዘን ውስጥ የገቡ ሴት ወገኖቻችንን በማሰብ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የሩቅ ምሥራቅ ሀገራት ሊቀ ጳጳስ እና የዓለም የሰላም አምባሳደር የሆኑት ብፅዕ አቡነ ያዕቆብ ከዚህ ጽሑፍ በታች የምታያዋትን በኀዘን ድባብ ውስጥ ያለች ወጣት ሴት ምስልን ከመንፈሳዊ ልጆቻቸው ዘንድ አግኝንና ካስተላለፉት መንፈሳዊ መልእክታቸው ጋር አብረን ልናጋራችሁ ወደድን፡፡

ብፁዕነታቸው በዚህች ኀዘንና ጭንቀት ክፉኛ የተጫናት በምትመስል ኢትዮጵያዊ ወገናችን፣ እህታችን ምስል ግርጌ ባሰፈሩት መልእክታቸውም፤ ጭንቀት እና ፍርሃት ከክፉ መንፈስ ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ፤ ‘‘ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፤ እግዚአብሔር የኃይልንና ራስን የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስን አልሰጠንም፡፡’’ ይላል፡፡

ስለሆነም የወንጌል ልጆቼ ይህን ወረርሽኝ መግታት የምንችለው በጸሎት፣ ከሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጠንን የጥንቃቄ ምክር ተግባራዊ በማድረግ፣ በመልካምነትና በፍቅር የበጎነት አገልግሎት ነው፡፡ በተጨማሪም በኮረና የተያዙ ወገኖቻችንን ባለማግለል ሕይወታቸውን በተስፋ እንዲሞላ በፍቅር ቀርበን በማጽናናት የተጋረጠብንን ችግር መቀነስ፣ መቋቋም ይቻለናል፡፡ በኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ጊዜ የሆነብን አሳዛኝ ታሪክ ዛሬም መደገም የለብንም፡፡

መቼም የወገኖቻችንን ጭንቀትና ፍርሃት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ከበሽታው ሥጋት ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጫናው ሌላው አስጨናቂ ጉዳይ እየሆነ ነው፡፡ በኮረና ምክንያት በቤተ እግዚአብሔር እንኳን በጋራ መሰባሰባችን እንዲህ ገደብ ሲጣልበት ሊያሳድርብን የሚችለው ጫና ከባድ ነው፡፡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችንና ማኅበራዊ መስተጋብራችን በመገደቡ የተነሳ ተጽእኖ ሊያሳድርብን እንደሚችልም እሙን ነው፡፡ በደስታም ሆነ በኀዘን ተሰብስበን እርስ በርሳችን የምንመካከርበት፣ ጥብቅ የሆነ ቁርኝት ያለው ማኅበራዊ መስተጋብራችን ሲቀዛቀዝና ሲቀር የሚሰማን ስሜት ከባድ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህን አጋጣሚ ራሳችንን ለመመርመር ለንስሓ ለፍቅርና ለበጎ ሥራ ብናውለው መልካም ነው፡፡ የቀደሙ አበው፤ ‘‘ወገን ቢረዳዳ ችግርም አይጎዳ’’ እንዲሉ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን በማጠናከር በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት፤ የእለት ጉርስ የዓመት ልብስ ለማግኘት የተቸገሩትን ወገኖቻችንን በመርዳት ይህን ክፉ ጊዜ በፍቅር አገልግሎትና በጸሎት ማሳለፍ ትልቅ መንፈሳዊ ዋጋ አለው፡፡

የወንጌል ልጆቼ የኮረናን ወረርሽኝ መከላከል፣ ብሎም ማጥፋት የምንችለው በጸሎት፣ ከሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጠንን የጥንቃቄ ምክር በመተግበር፣ እርስበርሳችን በፍቅርና በበጎ ሥራ በመደጋገፍ ነው፡፡ መጽሐፍ፤ ‘‘ማስተዋል ይጠብቅኻል፣ ጥንቃቄም ይጋርድኻል፤’’ እንዲል፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር ያላችሁ መንፈሳዊ ልጆቼ ጸሎታችንን አናቋርጥ፣ ከባለሙያዎች የሚሰጠንን የጥንቃቄ መልእክትም ሳንታክት እንተግብር፡፡

የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ!
የእመቤታችን፣ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎትና ምልጃ አይለየን!

የጽሑፍ ቅንብር ተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top