Connect with us

ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ 58 የባህል ሕክምና ናሙናዎች ተለዩ

ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ 58 የባህል ሕክምና ናሙናዎች ተለዩ
Photo: Facebook

ጤና

ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ 58 የባህል ሕክምና ናሙናዎች ተለዩ

“በኮሮና ቫይረስ እና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ አገር-በቀል የባህል ሕክምና ዕውቀቶች ሊያመጡ የሚችሉት መፍትሔዎች” በሚል ርእስ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሮችና የዘርፉ ምሁራን ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደገለፁት ከዚህ በፊት ወደ ምርምር ሂደት እንደገቡ የተገለጹት 58 የባህል ሕክምና ናሙናዎች በቅደም ተከተላቸው እየተሠሩ ነው፡፡ የቀረቡት የባህል ሕክምና ናሙናዎቹ የኮሮና ቫይረስን ቅድመ መከላከልና ከተያዙ በኋላ ለማከም የሚያስችሉ ተብለው በባለሙያዎች ተለይተዋል፡፡ መድኃኒቶቹ በማጨስ፣ በማጠን፣ በመቀባትና በመዋጥ በሚል እንደተከፈሉም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡ የአገር በቀል ዕውቀትን መጠቀም ግዴታ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ወደፊትም አገሪቷ በባህል ሕክምና መታወቅ መቻል እንዳለባት አመልክተዋል፡፡

በሳይንስ የተደገፈው ሕክምና ጥቂት ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ አገር በቀል ዕቀውቶች ለመዘናዊ ሕክምና መሠረት መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ የዘርፉ ባለሙያዎች መመርምር እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡ ‘‘በዘርፉ በቂ ዕውቀት እና ሀብት እያለን አዕምሯችን በምዕራባዊ ዕውቀት ጥገኛ ማድረግ የለብንም’’ ብለዋል ዶክተር ሂሩት፡፡
ማንኛውንም ባህላዊ መድኃኒት ወደ ዘመናዊ የመቀዬር አቅም እንዳለም የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
(አማራ መገናኛ ብዙሀን)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top