Connect with us

ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሊሰነዘር የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ

ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሊሰነዘር የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ ነን—የመከላከያ ሠራዊት
Photo: Facebook

ዜና

ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሊሰነዘር የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ

ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሊሰነዘር የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን የአገር መከላካያ ሠራዊት አባላት ለኢዜአ ገለጹ።

ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ከተጣለ ጀምሮ በአገር ውስጥ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በሕዝባዊ ተሳትፎ የሚደረገው ድጋፍ ወሳኝ የሚባል ደረጃ ላይም ደርሷል።

አጠቃላይ የግንባታው አፈጻጸም በአሁኑ ወቅት ከ73 በመቶ በላይ የደረሰው የሕዳሴው ግድብ በመጪው ክረምት ውኃ መያዝ እንዲጀምር ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በግድቡ ላይ የሚሰሩ ሥራዎች ለማስተጎጓል ግብፅ አንዴ በዲፕሎማሲው ሌላ ግዜ ደገሞ ማስፈራራትን እንደዋነኛ ስትራቴጂ አድርጋ ተንቀሳቅሳለች።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ይህ ዓይነቱ የግብፅ አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለው ነው የሚናገሩት።
ግድቡ የህልውና ጉዳይ እንደሆነ የሚገልጹት የሠራዊት አባላት ኢትዮጵያዊያን በጉጉት እንደ ዓይናቸው ብሌን የሚያዩት ፕሮጀክት መሆኑም አንስተዋል።

ከሠራዊት አባላት መካከል ሻምበል ግዛቸው አበበ “የቀደሙት አባቶች ቴክኖሎጂ ባለነበረበት ወቅት የአገርን ሉዓላዊነት አስጠብቀዋል፤ የግድቡ ጉዳይም ከዚህ ተለይቶ የሚታይ አይደለም” ይላሉ።

”በዚህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የሚደራደርና ውርደትን ለትውልድ አሳልፎ የሚሰጥ የለም” ያሉት ሻምበል አበበ፣ በዚህ በኩል ሠራዊቱ በማንኛውም ሰዓት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥትና ዜጎች እየተገነባ ያለው ግድብ በማንኛውም ኃይል ሊደናቀፍ አይችልም ያሉት ደግሞ ሌተናል ኮሎኔል ኃይላይ ፍሰሐ ናቸው።

ግድቡ የኢትዮጵያዊያን ቅርስ መሆኑን ያስታወሰው ወታደር ኃይሉ ምክረ በበኩሉ ”ድንበር ጠባቂ እንደመሆኔ ማንኛውንም ግዳጅ ተቀብዬ ለመፈጸም ቁርጠኛ ነኝ” ብሏል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top