Connect with us

ከ25 ሚልየን በላይ ኢትዮጵያውያን ለተረጅነት ተጋልጠዋል

ከ25 ሚልየን በላይ ኢትዮጵያውያን ለተረጅነት ተጋልጠዋል
Photo: Social media

ዜና

ከ25 ሚልየን በላይ ኢትዮጵያውያን ለተረጅነት ተጋልጠዋል

ከ25 ሚልየን በላይ ኢትዮጵያውያን ለተረጅነት ተጋልጠዋል

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከ25 ሚልየን በላይ ኢትዮጵያውያን ለእርዳታ ጠባቂነት መዳረጋቸውን የአለም የምግብ ኘሮግራም አስታወቀ።

ከዚህ ቀደም በድርቅና በተለያዩ ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች 15 ሚልየን ኢትዮጵያውያን የእርዳታ ጠባቂ እንደነበሩ ያወሳው ሪፖርቱ ተጨማሪ 10 ሚልየን ኢትዮጵያውያን በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የሰው እጅ ጠባቂ ሆነዋል።

በከተማ በዋንኛነት የኮሮና ወረርሽኝ ስጋት የረጅዎችን ቁጥር ማሳደጉን፣ በገጠር ደግሞ ከኮሮና በተጨማሪ የአንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ያደረሰው ጉዳት ተደማምሮ ለችግሩ መባባስ አይነተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ የአንበጣ እንዲሁም ድርቅና የጎርፍ አደጋዎች በመተባበር በሚልየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሰው እጅ ጠባቂ እያደረጉ መሆኑን የገለፀው የተቋሙ ሪፖርት የበለጠ ቀውስ እንዳይከሰት መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስቧል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር ብቻ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ሶስት ሚልየን ኢትዮጵያውያን ለተረጅነት ተዳርገው እንደነበረ፤ ይህ አሀዝ በየጊዜው እየጨመረ መሆኑን ጠቁሟል።

ባለፈው ሳምንት የኮሮና ወረርሽኝ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተቋቋመው የፀረ ኮሮና የሚኒስትሮች ኮምቴ ባካሄደው ስብሰባ ወቅት 30 ሚልየን ኢትዮጵያውያን ለተረጅነት ሊዳረጉ እንደሚችሉ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

(አዲስ አድማስ ግንቦት 29/2012 እትም)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top