Connect with us

ዓለም የሚናፍቀው ገበታችንና ድህረ ኮሮና ከሰባቱ የፎርቢስ መዳረሻዎች አንዷ

ዓለም የሚናፍቀው ገበታችንና ድህረ ኮሮና ከሰባቱ የፎርቢስ መዳረሻዎች አንዷ የኾነችው ኢትዮጵያ፤
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ዓለም የሚናፍቀው ገበታችንና ድህረ ኮሮና ከሰባቱ የፎርቢስ መዳረሻዎች አንዷ

ዓለም የሚናፍቀው ገበታችንና ድህረ ኮሮና ከሰባቱ የፎርቢስ መዳረሻዎች አንዷ የኾነችው ኢትዮጵያ፤

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የፎርብስ መጽሔት ከኮሮና በኋላ የሰው ልጅ ከሚጎበኛቸው ስፍራዎች አንዷ አድርጎ ኢትዮጵያን አስቀምጧታል፡፡ ዓለም ገበታችንን ይናፍቃል ሲል የፎርቢስን ዘገባ እንዲህ ተመልክቶታል፡፡) l ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

መቼም ፎርብስ ጣቱን ዘርግቶ አንድ ብሎ ሲቆጥር ቁጥር ውስጥ እንደ መግባት ሸጋ ነገር የለም፡፡ ይኼ ዓለም አቀፋዊ ሚዲያ ድህረ ኮሮና መታየት ያለባቸውን ሰባት ሀገራት አስቀምጧል፡፡ አንዷ የኔ ሀገር ናት፡፡

ያሬድ ራናሃን በፎርብስ ላይ ያስቀመጣቸው ሰባት ሀገራት ቀን አልፎ እድሜ ከሰጠው የሰው ልጅ ቢያያቸው ብሎ የለያቸው ናቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ሀገር ምክንያቱን አስቀምጧል፡፡ አፍሪካን ከመሰረቱ 54 ሀገራት አንዷ ናት ያላት ኢትዮጵያ የአስደናቂ ታሪካዊ ዳራ ባለቤትነቷን መስክሯል፡፡

ራናሃን ምስክርነቱን ሲሰጥ ኑ እንጂ ብዙ ነገር ታያላችሁ ሲል ሀገሬን አወድሷታል፡፡ የተፈጥሮ ውበቷ፣ የተራሮቿን ገጽታዎች፣ የበለጸገው ታሪኳን ቀጠሮ መያዝ ላለባቸው ጎብኚዎች ነግሯቸዋል፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ብሎ ያስቀመጠው ግን የኢትዮጵያን ገበታ ነው፡፡

በእጅ እራት መብላትን ልዮ ስፍራ ሰጥቶታል፡፡
ሁሉም ሰው በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ይኼንን በእጅ እራት የሚበላበትን የኢትዮጵያ ገበታ እንዲሳተፍም ባህላዊ እሴቱን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አንድ ምክንያት አድርጎ አስቀምጦታል፡፡

ሀገሪቱ ለታሪክ ጸሐፊዎች እውነተኛ ደስታ ናት የሚላት ኢራንን ደግሞ ሌላው መጎብኘት ያለባት ሀገር ከሆኑት ተርታ ውስጥ ቆጥሯታል፡፡ ጆርጂያና በርማም ከሰባቱ አብረው የተቆጠሩ ናቸው፡፡

ደሴቷን ምድር ፊሊፒንስን አወድሶ ጤና ሰጥቶት ዓለም ከኮሮና በኋላ ይመለከታት ዘንድ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ቆጥሯታል፡፡ ሌላኛዋ ሀገር ስሎቫኒያ ናት፡፡ ስሎቫኒያን ሲጎበኙ ወደ ስሜናዊ ክፍሏ ጎራ ብለው የጁሊየስ ተራሮችን ለመጎብኘት መጓዝዎን እርግጠኛ ይሁኑ ሲል መስክሯል፡፡

ስሜን አፍሪቃዊቷ ሀገር ቱኒዚያም ከሰባቱ መዳረሻዎች አንዷ ናት፡፡ አፍሪቃ ከሰባቱ ጥቆማዎች ሁለቱን ወስዳለች፡፡ በእርግጥም የሜዲትራኒያን ዳርቻዋ ሀገር ለታሪክ አድናቂዎች፣ ወደ ሰሃራ በረሃ መጓዝ ለሚሹ ጀብደኞችና ድንቅ ነገር ማየት ለሚሹ ጎብኚዎች አንዷ ናት ብሏታል፡፡ እኛስ ከኮቪድ 19 በኋላ የት ይኾን ለመጓዝ ያሰብነው?

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top