Connect with us

ግንቦት ሃያ የደስታ ወይስ የሀዘን ቀን?

ግንቦት ሃያ የደስታ ወይስ የሀዘን ቀን፤ ደርግን ለመጣል ያልሞከረው ማን ነው?

ማህበራዊ

ግንቦት ሃያ የደስታ ወይስ የሀዘን ቀን?

ግንቦት ሃያ የደስታ ወይስ የሀዘን ቀን፤ ደርግን ለመጣል ያልሞከረው ማን ነው?
******
ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ግንቦት ሃያ ቀን ጥሎታል፤ ዛሬ እንደ ትናንቱ የአደባባይ በዓል ሆኖ አይከበርም፡፡ በየቀበሌው በሚቀርቡ መኪኖች ተጭኖ መስቀል አደባባይ መሄድ የለም፡፡ ግንቦት ሃያን የማደብዘዙ ነገር ውሎ አድሮ ግንቦት ሃያ ምናችን ነው የሚል መንፈስ እየታየ መጣ፡፡ እርግጥ ለዚህ ትውልድ ግንቦት ሃያ ምኑም ሊሆን ይችላል ለዚያ ትውልድ ግን እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል?

ደርግን ለመጣል ያልሞከረው ማን ነው? እዚህ ሀገር ደርግም ንጉሡም ልክ ናቸው የሚሉ የርዕዮተ ዓለም ሰካራሞችን አይተናል፡፡ የደርግ ስርዓትን አፍቅሮ ባላባታዊ ሥርዓቱን ልክ ነበር ማለት ስካር ነው፡፡

ደርግን ለመጣል ያልሞከረው ማን ነው? የቀድሞው ባላባቶች እኮ ኢዲዮ ነን ብለው መሳሪያ አንስተውበታል፡፡ እንደ ደጃዝማች ጸሐይ እንቁስላሴ ያሉት ደርግን የታገሉት የመርሐቤቴን ህዝብ ይዘው አይደል እንዴ? መኢሶንም በኋላ ይለጠፍ እንጂ ደርግን ለመጣል ከመቋመጥ ቤተ መንግስት የታከከ ፓርቲ ነው፡፡ ኢህአፓ አሲንባ የገባው ደርግ ቤተ መንግስት ተመችቶት እንዲኖር ነው እንዴ?

ደርግ ከኢሰፓ ውጪ በትውልዱ ፓርቲዎች በሙሉ ያልተፈለገ፣ የትውልዱ ፓርቲ በሙሉ የቻለ በመሳሪያ ያልቻለ በጥላቻ ያሳደደው መንግስት ነው፡፡ ግንቦት ሃያ እውን እንዲሆን ያልታገለው ማን ነው? የጠለምት ህዝብ ልጁን አልሰጠም፤ የዳግጉር ጉምዝ ከኢህአፓ ጋር አልቆመም፣ ቋረኛ እንቢኝ ብሎ እስከ 1983 ከኢህአፓ ጋር ሙጥኝ ያለው ደርግን አፍቅሮ ነው፡፡

ደርግን የጠላው የሻቢያና የህወሃት መንፈስ ብቻ ተደርጎ የሚቆጠው ነገር መደጋገም ሲጀምር እውነት መምሰል ጀመረ፡፡ እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ ደርግ በራሱ የሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች መፈንቅለ መንግስት ጭምር የተሞከረበት መንግስት ነው፡፡

ደርግን በመጣል በኩል እንደ ትግራይ እናት የበለሳ እናት ልጇን ገብራለች፡፡ የበየዳ ሰው አልቋል፡፡ የዋግ ወጣት ሜዳ ቀርቷል፡፡ የደርግ ሥርዓት በጎንደር አንድ ትውልድ ቅርጥፍ አድርጎ የበላ ነው፤ በጅማ ትንታግ ትውልድ ሜዳ ያስቀረ ነው፡፡ ዛሬ ለገባንበት የመከራ ዘመን በራፍ ነው፡፡ አሚሩ ከአፋር የተሰደዱት ደርግን አፍቅረው ነው?

ደርግ የወደቀበት ቀን በምን አግባብ የህወሃት በዓል ብቻ ይሆናል? ኢጭአቱስ? ደርግን የደቡብ ወጣቶች አልታገሉትም?

እንደ አረጋሽና ነጻነት ሁሉ እነ አያልነሽም ታግለውታል፡፡ እንደ አባይ ጸሐዬ ሁሉ አሰፋ ጫቦም ገጥሞታል፡፡ እንደ ቀሺ ገብሩ ሁሉ መሬው ደጃዝማች እንቢኝ ብለውታል፡፡

ደርግ ወደቀ፤ ደርግ የወደቀበት ቀን እንዴት የህወሃት ብቻ ተደርጎ ይቆጠራል? ደርግን ለመጣል ያልታገለ ጸጋዬ ደብተራው ነው? ብርሃነ መስቀል ረዳ? ሃይሌ ፊዳ ነው? ነገደ ጎበዜ? ደርግ ሁሉም የጣሉት መንግስት፤ ደርግ ግንቦት ሃያ የወደቀ ስርዓት፡፡

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top