Connect with us

ሊፈርስ ነው፤ በሦስት ቀን ለቃችሁ ውጡ ተብለናል

ሊፈርስ ነው፤ በሦስት ቀን ለቃችሁ ውጡ ተብለናል

ባህልና ታሪክ

ሊፈርስ ነው፤ በሦስት ቀን ለቃችሁ ውጡ ተብለናል

ቤቱን እየተገለገሉበት ያሉት ሰዎች ትዕዛዝ የደረሳቸው በቃል ነው፡፡ ሊፈርስ ነው፤ በሦስት ቀን ለቃችሁ ውጡ ተብለናል ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ሰባቱ ቅርስ ቤቶች ይለማሉ እንጂ አይፈርሱም ሲል በፌስ ቡክ ገጹ አስፍሯል፡፡
******
በአዲስ አበባ የሚገኘው እና የዳግማዊ ምኒልክ የግራ ወንበር ዳኛ የተክለማርያም ባሻ መኖሪያ የነበረው 112 ዓመት ያስቆጠረ ቅርስ ሊፈርስ ነው ለቃችሁ ውጡ መባላቸውን በተመለከተ የቀረበው የድሬ ቲዮብ ዘገባ ሀሰተኛ እንደሆነ የሚገልጽው ዘገባ ሀሰተኛ መረጃ ሳይሆን ቤቱን ከሚገለገሉበት ሰዎች የደረሰ መረጃ ነው፡፡

የቤቱ ነዋሪ ከመንግስት መጣን ያሉ ሰዎች እንዳስፈራሯቸው ገልጸው በሦስት ቀን ውስጥ ለቀው እንዲወጡ በቃል ትዕዛዝ ሰጠዋቸዋል፡፡ ለትዕዛዙ ህጋዊነት ደብዳቤ ሲጠይቁም በዛቻ እናስርዎታለን ተብያለሁ ነው የሚሉት፡፡

ይሄንን ተከትሎ ወደ ሚዲያ የወጡት ግለሰብ ቤቱን ሲገለገሉት የነበረው የኒዮን አዲስ ባለቤት ወይዘሮ ቅድስት ጌታቸው መረጃውን ይፋ ካደረጉ በኋላ የሚለቁበትን ዓላማ ከፌስ ቡክ አንብበዋል፡፡ ያም ሆኖ ትናንት ምሽት ድረስ ለድሬ ቲዮብ ዘጋቢ ወይዘሮ ቅድስት ይፈርሳል፡፡ ቅርስ እያልሽ አትቀባጥሪ የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ነው በድጋሚ ያረጋገጡት፡፡

እንዲፈርስም ሆነ እንዲታደስ የተወሰነው ውሳኔን የተመለከተውን ህጋዊ እርምጃ እንደ ዜጋና ቤቱን ለረዥም አስርት ዓመታት እንደያዘ ግለሰብ አንዳችም ህጋዊ ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው የሚገልጹት ወይዘሮ ቅድስት ውላቸው ከኪቤአድ ጋር ቢሆንም ከኪቤአድ በኩል የተገለጸላቸው ነገር እንደሌለ ገልጸውልናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክረተሪያት በበኩሉ ከመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት ባለው አዲስ አበባን መልሶ የማልማትና የማስዋብ ስራ ፕሮጀክቱ በሚያልፍበት መስመር ሰባት በቅርስነት የተመዘገቡ ህንጻዎች በመልሶ ማልማት ውስጥ የሚካተቱ እና ይዘታቸውን ጠብቀው የሚታደሱ መሆናቸውን ገልጾ አይፈርስም ሲል በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

ህንጻዎቹን የሚገለገሉባቸው ሰዎችም ወደሌላ ስፍራ የሚዛወሩ ይሆናል ብሏል፡፡ ከህንጻዎቹ የአንዱ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ቅድስት ግን በአስቸኳይ ለቀሽ ውጪ ተባልኩ እንጂ ለምን ዓላማና የት መሄድ እንዳለብኝም አልተገለጸልኝም፡፡ ለቀሽ ውጪም የተባልኩት ከኪቤአድ ወይም ከከተማ አስተዳደሩ በተጻፈ ደብዳቤ ሳይሆን በቡድን ወደ ቢሮዬ በመጡ ሰዎች ነው ሲሉ ለድሬቲዮብ ገልጸዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top