Connect with us

ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ ተያዘች

ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ ተያዘች

ህግና ስርዓት

ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ ተያዘች

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን ይዛ በመሰወር የማስለቀቂያ 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ መያዟን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ግለሰቧ ድርጊቱ ፈጽማለች የተባለው ግንቦት 10/2012 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ በወረዳው ሙሴ ባንብ በተባለ ከተማ ከግለሰብ ቤት በሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ነው።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አንተነህ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለፁት ግለሰቧ ከግብረአበሯ ጋር በመሆን ህፃኑን ይዛ በመሰወር ለህፃኑ ወላጅ 600 ሺህ ብር ከከፈሉ ልጃቸውን ልትመልስ እንደምትችል በስልክ ደውላ ታሳውቃለች።

የወረዳው የፀጥታ አካል ህፃኑን ይዛ የሄደችበትን አካባቢ ፈጥኖ በማጣራት ባደረገው ጥብቅ ክትትልና አሰሳ ትናንት በወገራ ወረዳ ግራርጌ በተባለው የገጠር ቀበሌ መያዝ መቻሉን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት ህፃኑን ወላጆች እንዲረከቡ መደረጉንና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በድርጊቱ በዋናና በተባባሪነት የተሳተፉት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ ሂዳት ላይ እንደሚገኝ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ገልጸዋል።

በድርጊቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሌሎች ሶስት ግለሰቦችም ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

በማህከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ በሰው ማገት ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን ባለፈው ሳምንት ተዘግቧል፡፡

ምንጭ:- ኢዜአ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top