Connect with us

በአዲስ አበባ የኮሮና ስርጭት የገነነበት አንድ መንደር …

በአዲስ አበባ የኮሮና ስርጭት የገነነበት አንድ መንደር ሙሉ በሙሉ ከቤት መውጣት ተከለከለ
Photo: Facebook

ዜና

በአዲስ አበባ የኮሮና ስርጭት የገነነበት አንድ መንደር …

በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ተጨናንቆ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች በአንዱ ፣ አብነት አካካቢ፣ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ሲባል ሙሉ በሙሉ አንድ መንደር ውሽባ እንዲገባ ተደርጎ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ መከልከሉን የዋዜማ ሪፖርተር በስፍራው ተገኝታ ተመልክታለች።

በልደታ ክፍለከተማ አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ግለሰቡ በተጎዳኝ ህመሞች ለረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ህይወታቸው አልፎል ፡፡ ቀድሞ የተወሰደው ናሙና ሟቹ ግለሰብ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማሳየቱ ከሳቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ ምርመራና ክትትል ተደርጎ 32 ስዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከባለሙያዎች ስምተናል።

ይህንን ተከትሎም በወረዳው (አብነት አካካቢ) 500 አባወራ የሚገኝበት መንደር ከእንቅስቃሴ ታግዶ ተዘግቶል፡፡ ወደ መንደሩ በሚያስገባው ቅያስ ላይ ፖሊሶች እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ቆመው ከነዋሪው ሌላ ሰው እንዳያልፍ ሲከለክሉ ተመልክተናል፡፡

ለነዋሪው የአስቤዛ ፤የፅህና መጠበቂያ ሳሙና ፤ሳኒታይዘር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ አቅርቦቱ ከዚህ በፊት ለወረርሽኙ ተብለው ከተለያዩ አካላት ከተሰበሰበው እየተሸፈነ እንደሚገኝ ዋዜማ ተረድታለች በተለይም የአሊባባ ድጋፍ በእጅጉ እንዳገዘ የወረዳው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

የስራቸው ሁኔታ ግድ ከቤት የሚያስወጣ ለሆነባቸው ነዋሪውች ለሚሰሩበት ተቋም የትብብር ደብዳቤ እየተፃፈ ነው፡፡በዚህ መንደር የሚኖሩት ነዋሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እዛው ባሉበት ተወሽበው በመቆየት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የታለመ ነው፡፡ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ግንዛቤ ለማስጨበጥ በተቋቋመው አደረጃጀት ውስጥ ያሉ በጎ ፍቃደኞችም የችግሩ ሰለባ ናቸው።በዚያው ክፍለከተማ አምስተኛ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና ጉዳይ በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንክኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት 66 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለከተማ እና ልደታ ክፍለከተማ ጤና ሚኒስቴር ፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ለዚህ ሲባል የተቋቋመው ግብረሃይል ከዚህ የበለጠ እንዳይሰራጭ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት በልደታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሁሉም ህንፃዎች ላይ ምርመራ ተደርጎል፡፡ ምርመራውን ሲሸሹ የነበሩ ሰውችንም ተመልክተናል፡፡

እስካሁን (ቅዳሜ ግንቦት 15 ድረስ) ባለው መረጃ በልደታ ክፍለ ከተማ 104 ሰው በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ደግሞ 280 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ይህም ከሌሎቹ ክፍለ ከተሞች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ነው፡፡ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 11 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ [ዋዜማ ራOne of the slum areas of Addis Ababa PHOTO- FILE
ዋዜማ ራዲዮ- በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ተጨናንቆ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች በአንዱ ፣ አብነት አካካቢ፣ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ሲባል ሙሉ በሙሉ አንድ መንደር ውሽባ እንዲገባ ተደርጎ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ መከልከሉን የዋዜማ ሪፖርተር በስፍራው ተገኝታ ተመልክታለች።

በልደታ ክፍለከተማ አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ግለሰቡ በተጎዳኝ ህመሞች ለረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ህይወታቸው አልፎል ፡፡ ቀድሞ የተወሰደው ናሙና ሟቹ ግለሰብ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማሳየቱ ከሳቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ ምርመራና ክትትል ተደርጎ 32 ስዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከባለሙያዎች ስምተናል።

ይህንን ተከትሎም በወረዳው (አብነት አካካቢ) 500 አባወራ የሚገኝበት መንደር ከእንቅስቃሴ ታግዶ ተዘግቶል፡፡ ወደ መንደሩ በሚያስገባው ቅያስ ላይ ፖሊሶች እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ቆመው ከነዋሪው ሌላ ሰው እንዳያልፍ ሲከለክሉ ተመልክተናል፡፡

ለነዋሪው የአስቤዛ ፤የፅህና መጠበቂያ ሳሙና ፤ሳኒታይዘር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ አቅርቦቱ ከዚህ በፊት ለወረርሽኙ ተብለው ከተለያዩ አካላት ከተሰበሰበው እየተሸፈነ እንደሚገኝ ዋዜማ ተረድታለች በተለይም የአሊባባ ድጋፍ በእጅጉ እንዳገዘ የወረዳው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

የስራቸው ሁኔታ ግድ ከቤት የሚያስወጣ ለሆነባቸው ነዋሪውች ለሚሰሩበት ተቋም የትብብር ደብዳቤ እየተፃፈ ነው፡፡
በዚህ መንደር የሚኖሩት ነዋሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እዛው ባሉበት ተወሽበው በመቆየት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የታለመ ነው፡፡ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ግንዛቤ ለማስጨበጥ በተቋቋመው አደረጃጀት ውስጥ ያሉ በጎ ፍቃደኞችም የችግሩ ሰለባ ናቸው።

በዚያው ክፍለከተማ አምስተኛ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና ጉዳይ በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንክኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት 66 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለከተማ እና ልደታ ክፍለከተማ ጤና ሚኒስቴር ፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ለዚህ ሲባል የተቋቋመው ግብረሃይል ከዚህ የበለጠ እንዳይሰራጭ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት በልደታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሁሉም ህንፃዎች ላይ ምርመራ ተደርጎል፡፡ ምርመራውን ሲሸሹ የነበሩ ሰዎችንም ተመልክተናል፡፡

[ዋዜማ ራዲዮ]

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top