Connect with us

ዓለም አቀፍ የዘረፋ ወንጀል ከሸፈ

ዓለም አቀፍ የዘረፋ ወንጀል ከሸፈ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ዓለም አቀፍ የዘረፋ ወንጀል ከሸፈ

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማጭበርበር እና ዘረፋ ወንጀል አከሸፈ።

ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ረጅም ጊዜ በመውሰድ በተለያየ መንገድ ክትትል ሲያደርግበት የነበረው እና በጉዳዩም ላይ በቂ መረጃ ሲያሰባስብበት የቆየው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓትን በመጠቀም 110 ሚልዮን ዶላር የማጭበርበር እና የዘረፋ የወንጀል ሙከራ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጓል።

ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ በላከው መግለጫ ተጠርጣሪዎቹ ነዋሪነቱ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሆነው ኒል ቻርለስ የተባለ ግለስብ ስም በባንክ የተቀመጠ 110 ሚልዮን ዶላርን የባንክ ሒሳብ ባለቤቱ እንዳዘዘ አስመስለው አዲስ አበባ ከተማ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ተብሎ ከሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማውጣት የተለያዩ የማጭበርበር ስልቶችን ሲያቀናጁ እንደነበር አስታውቋል።

ይሁንና ሕገ ወጥ የገንዘብ ማዘዋወር እና ዘረፋ ወንጀሉ በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ስር የነበረ በመሆኑ፣ ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓ.ም በመጀመሪያ ዙር 60,990,939ብር ከተጠቀሰው ባንክ አውጥተው በማዳበሪያ ጭነው ባዘጋጁት ተሽከርካሪ ሊወስዱ ሲሉ ቀድሞም በጥብቅ ክትትል ስር ስለነበሩ እዚያው ባንክ ውስጥ እያሉ በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ብሏል። ወንጀሉን በማቀነባበር ከሚታወቁት መካከል አድይሚ አድርሚ አብዱልራፊ የተባለ ናይጄሪያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ሸገር እንግዳ ማረፊያ በቀን 450 ብር እየከፈለ ከአንድ ዓመት በላይ በመቀመጥ ተልእኮውን ለማስፈጽም ሲንቀሳቀስ እንደነበር ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲያካሂድ በነበረው ክትትል አረጋግጧል። #EBC

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top