Connect with us

በብዙ ቋንቋዎች ወንጌልን የተናገረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን

ፓርላማ ተናግሮበት በማያውቀው ቋንቋ ወንጌልን የተናገረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፤ እድሜ ለኮሮና መልካሙን አሳየን
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

በብዙ ቋንቋዎች ወንጌልን የተናገረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን

ብሔር ብሔረሰቦች ነገሱበት የተባለው ፓርላማ ተናግሮበት በማያውቀው ቋንቋ ወንጌልን የተናገረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፤ እድሜ ለኮሮና መልካሙን አሳየን፤
******
ከስናፍቅሽ አዲስ
መደበኛው የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ብዙ ነገር አሳይቶናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስትታማ የነበረችው በአህዳዊነት ቢሆንም ወቅት እውነት ይገልጻልና ብዝሃነቷ ታየ፡፡ በብዙ ቋንቋዎች ወንጌልን ሰበከች፤ ስትከሰስ ኖራለች፤ ከሳሾቿ ከነመኖሩ በማያውቁት ህዝብ ቋንቋ ግን ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን ሰብካለች፡፡ የቋንቋ ፌዴራሊዝም ነኝ የሚለው መንግስት ለሚዲያ ባላበቃው ቋንቋ በሚዲያ አስተምራለች፡፡

ብሔር ብሔረሰቦች ነግሰውበታል በተባለው ፓርላማ ተነግሮና ተደምጦ የማይታወቅ ቋንቋ ጭምር ወንጌል የተነገረበት አገልግሎት አሳይታለች፡፡ ከሳሽዎቿ ብዙ ሲያብጠለጥሏት በዝምታ ያለፈችው እንዲህ ካለው ወቅት ጋር እስክትገናኝ ነበር፡፡

ዛሬም ቋንቋ ሃይማኖት የሚመስለው ሰው ለምን በእኛ ቋንቋ ተሰበከ ብሎ ቋንቋው ሃይማኖተኛ አድርጎ የተመለከተ አድምጠናል፡፡ የእኔ እምነት በእኔ ቋንቋ ስላልተሰበከ ለምን ኦርቶዶክስ በኔ ቋንቋ ሰበከች ብሎ የከሰሰም አድምጠናል፡፡

በአጭር ጊዜ 28 ቋንቋዎችን ተጠቅማ አስተምራለች፡፡ የከሰስዋት አንገቷን አልደፉም፤ ቋንቋውን አብጠለጠሉ፡፡ በተለየ መልኩ የለውጥ ሃይሉ የፌዴራሉ የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ በወሰናቸው የአማርኛ ትግርኛ ሱማሊኛና አፋርኛ ቋንቋዎች ብሔራዊ ክብርን አሳይታ አስተምራለች፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የውጪ ዜጎች በሚሰሙት እንግሊዘኛ እምነትና ጽናት ተሰብኮላቸዋል፡፡ በጋሞኛ፣ በዎላይተኛ፣ በጉራጊኛ፣ በሲዳምኛ፣ በሶዶ ክስታኔ፣ በጉምዝኛ፣ በከንባትኛ፣ በኽምጠኛ /አገው/፣ በአዊኛ፣ በከፍቾ፣ በሐዲይሳ፣ በቡርጂኛ፣ በጌዶኦፋ፣ በዛይሴኛ፣ በየምሳ፣ በማሌ፣ ቤንች፣ ሐመርና አኝዋ ቋንቋዎች ህዝቡን ተጠንቀቁ፣ ጸልዩ፣ ጽኑ፣ በንስሐ ተመለሱ ብላለች፡፡

ይሄ ከምታስበው ከምትመኘው መሆን ከምትፈልገው ትንሹ ነው፡፡ እድልና ጊዜ ወደ ፊት ቤተ ክርስቲያኗ በታማችባቸው ነገሮች ሀሰትነት ተገልጣ እንደምትታይ አምናለሁ፡፡ ከሳሽዎቿ ዛሬም ምክንያት ፍለጋ ሲደክሙ እሷ ብሔራዊ ኩራትነቷን አላስነጠቀችም፡፡ ከጫፍ ጫፍ በሀገር ባህል፣ ወግ ቋንቋና ሥርዓት ህዝብን ትታደጋለችና፤

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top