Connect with us

መንግስትነት ክብሩ የት ነው?

መንግስትነት ክብሩ የት ነው?
Photo: Social Media

ነፃ ሃሳብ

መንግስትነት ክብሩ የት ነው?

አራት ኪሎ መኖር፣ ፓርላማ መቀመጥ፤ ዜጋን ካልጠበቁ፤ መጦር እንጂ መምራት አይደለም፡፡
አንድ መንደር ከአንድ ሽፍታ ነጻ ማውጣት ከብዶ ግብጽ ላይ መፎከር፤
******
(ከስናፍቅሽ አዲስ)

ማንም ሀገር መምራት ባይችል ምክንያት አያጣም፡፡ ሀገር መምራት ማለት ምክንያትን አሸንፎ ችግርን መፍታት ነው፡፡ ለሁሉም ምክንያት ሰጥቶ ችግሩን አለመፍታት ችግር ፈጣሪው ካደረሰው ሰቆቃ የማይተናነስ ድርሻ አለው፡፡

መንግስትነት ክብሩ የት ነው? ዜጋን መታደግ ላይ አይደለም እንዴ? ፍትሕ በሌለባት ሀገር መንግስት ነኝ ማለት ምንስ ረብ አለው? ዛሬ ፓርላማው ያሳየው ቁጭት የሚመሰገን ነው፡፡

በዛሬ ማብቃት የለበትም፡፡ ዛሬ የምትወስኗት ውሳኔ ነገ ልጆቻችሁና የልጅ ልጆቻችሁ የሚኖሩበትን ሀገር ይሰራል፡፡ ወይም ከእናንተ ባልተፈጠርን ብለው የሚጸጸቱ ልጆች ወላጆች ትሆናላችሁ፡፡ በሰው ደም በምትጨማለቅ ሀገር ብልጽግና ሰብኮ በልቶ ማደር የገዳይ ያኽል ነው፡፡

ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች መደበኛው አጀንዳ ላይ መወያየት እንደማይፈልጉ በመግለጽ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዛቸውን ስሰማ ልቤ ይበልጥ የተጎዳው ቀድሞስ ግድያውን እንደ ሰርግ ሆኖ መደበኛ አጀንዳ ይዞ የቀረበው አካል እጁ መሳሪያ ቢጨብጥ የማይገድል መንፈስ እንዳለው በምን አምናለሁ፤

በመንግስት በኩል ያለው እኛን መሳይ ሀዘን ነገን ያሳየናል ብዬ አላምንም፤ ይልቁንም በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዘር ጥቃቱ የሚሳተፉትንና በሰለጠነው ዓለም የተሸሸጉትን ጭምር በማጋለጥ የሽብርተኞችና የገዳይ ቡድኖች ስብዕና ዓለም እንዲያውቀው፤ አይዞህ ባያቸውን በዓለም ህግ እንዲጠይቅ እንቅስቃሴ ያስፈልጋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ከዛሬ ነገ ይቀረፋል ብለው ያዩትና ከቡራዮ እስከ ወለጋ የዘለቀው የሁለት አመት ዘር ተኮር ጭፍጨፋ አሁን ደረጃውን አሳድጎ ቦታውን አስፍቶ የትም የሚሰማ መራር ዜና ሆኗል፡፡ ይሄንን ማቆም የልጆቻችንን ሀገር መፍጠር ነው፡፡

መንግስት አለሁ ካለ ለእኛ ብሎ ሳይሆን ቢያንስ ስናልቅና ሲከፋ ተረኛው እሱ ነውና ራሱን ያድን፤ ግብጽ ላይ ከመፎከር በራሱ ሜዳ መምራት ያቃተውን ጫካና ዱር ይቆጣጠር፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን ማንንም ባለመጠበቅ፤ ማንም ማንንም የማይገድልበትን ሀገር ለመፍጠር አብረን እንቁም፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top