Connect with us

ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ በረከት ስሞኦንና አቶ ታደስ ካሳን የቅጣት ማቅለያ አዳመጠ

ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ በረከት ስሞኦንና አቶ ታደስ ካሳን የቅጣት ማቅለያ አዳመጠ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ በረከት ስሞኦንና አቶ ታደስ ካሳን የቅጣት ማቅለያ አዳመጠ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአቶ በረከት ስሞኦን እና አቶ ታደስ ካሳን የቅጣት ማቅለያ እንዲሁም የዓቃቤ ህግን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት አዳመጠ።

ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት በዋለው ችሎት ዓቃቤ ህግ አቶ በረከት ስሞኦንና አቶ ታደስ ካሳ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በነበሩ የስራ ውሎች የጥረት ኮርፖሬት ጥቅምን በሚጎዳ መንገድ ተንቀሳቅሳዋል በሚል የቀረባቸውን አራት ክሶች መርምሮ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም አቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የቃልና የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሁም ተከሳሾች የቀረቧቸውን የቃልና የሠነድ መከላከያ ማስረጃዎችን መርምሮ በአቶ በረከትና አቶ ታደሰ ካሳ በተከሰሱበት ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ወንጀል የጥፋተኝነት ውሳኔ መወሰኑም ይታወቃል።

በዚህም የፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ ህግ ድንጋጌ 703 /1 ሀ እና ለ መሠረት አቶ በረከት ስሞኦንና አቶ ታደሰ ካሳ በተከሰሱባቸው 1ኛ እና 2ኛ ክሶች ጥፋተኛ ሲባሉ በ3ኛው ክስ ደግም ሁለቱም ነፃ ተብለዋል።
በተጨማሪ አቶ በረከት በ4ኛው ክስም ነፃ ሆነዋል።

በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎም ዓቃቤ ህግ እና ተከሳሾች ያቀረቡትን የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ አዳምጧል።
ተከሳሾቹ በጠበቃቸው በኩል የቤተሰብ አባል መሆናቸው፣ ህመምተኛ መሆናቸውን፣ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የወንጀል ድርጊት አለመፈፀማቸውን እና በመንግስት እና በፖለቲካ ስራ ለበርካታ ዓመታት ማገልገላቸውን በማቅለያነት አቅርበዋል።

በተጨማሪም በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ድንጋጌ 703/1 ሀ እና ለ የተጠቀሰው የወንጀል ዓይነት ከፍተኛ ጥፋት የሚጠይቅ በመሆኑ በ702 እንዲታይልን ሲሉም ጠይቀዋል።

አቃቤ ህግ በበኩሉ ተከሳሾቹ በመንግስት እና በፖለቲካ ስራ ማገልገላቸው ህጉን ከሌላው ሰው የበለጠ እንዲያውቁ የሚያደረግ በመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ድንጋጌ 703/1 ሀ እና ለ ሊጠየቁ ይገባል ሲል የቅጣት ማክበጃውን አቅርብል።

ችሎቱም የግራ ቀኙን ተመልክቶ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓመት ምህረት ቀጠሮ ሰጥቷል።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top