Connect with us

በመረጥነው ስላልተመራን ለመረጠን መሪ ለመታዘዝ አይከብደንም

በመረጥነው ስላልተመራን ለመረጠን መሪ ለመታዘዝ አይከብደንም
Photo Facebook

ፓለቲካ

በመረጥነው ስላልተመራን ለመረጠን መሪ ለመታዘዝ አይከብደንም

ምርጫ የማናውቀው ሀገር ነው፤ በመረጥነው ስላልተመራን ለመረጠን መሪ ለመታዘዝ አይከብደንም፡፡
ዶክተር አብይ ላይመቸን ይችላል ያለ ወንበር እንዳጠፉን ተቃዋሚዎች ግን አይጨክንብንም፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

የአቶ ልደቱና የጃዋር ሀሳብ የግል ምኞትና የዘለዓለም ናፍቆታቸው ሊሆን ይችላል፡፡ አቶ ልደቱ በመረጥነው ተመርተን እንደማናውቅ ለታሪክ ያስቀመጣቸው ምልክት ናቸው፡፡ እኛ መርጠን አናውቅም ድምጻችን ውሎ አድሮ ጦስ የሚያመጣብን ህዝቦች ነን፡፡ ከምርጫ በኋላ ግብዣችን ጥይት ነው፡፡

እኛ ልብ ያለው ተቃዋሚም አጋጥሞን አያውቅም፡፡ የእኛ ሀገር ተቃዋሚ በመከራው ጊዜ አናየውም፤ በችግር ሰዓት ዋሻው ውስጥ ይገባል፡፡ ብዙ መክሮን እንዴትና በምን መልኩ መንግስትን እንደምንጥለው አቅጣጫ ሰጥቶን እኛ አደባባይ ስንውል እሱ ፓርላማ የሚገባ ራስ ወዳድ ነው፡፡ ቢጨክንም መልካም ቢሆንም ጥሩ ግንኙነት ያለን ከማንመርጠው መንግስት ጋር ነው፡፡

ትናንት ሳንመርጠው የመራን ኢህአዴግ ቢያንስ አባይን ገድቧል እሱ አባይን ሲገድብ ብር አታውጡ ብሎ ከግብጽ ጋር የቆመ ተቃዋሚ ዛሬ በሀገሬ ፍቅር ተቃጠልሁ ሲል ስንሰማ “ትዝታ አያረጅምን” ጋብዘን አብሮ ከመደነስ በስተቀር ምን ምርጫ አለን፤

ዛሬም ምርጫ ለእኛ የማያውቁት ሀገር ነው፤ የመረጥነውን በማንበላበት ሀገር ስለ ግብርናው ስለ ጤናው ስለ እጅ መታጠቡ የሚጨነቅ፣ ሲፈልግ ገርፎ ሲፈልግ ተቆጥቶ ሀገርን ከመፍረስ የሚታደግ፣ ጥቂቶችን ስልጣን ነፍጎ ብዙሃን ከወሮበላ መፍንጫነት እንዲጠበቁ የሚተጋ መንግስት ካገኘን ባንመርጠውም ምርጫችን ነው፡፡

ዶክተር አብይ ለብዙ ሰዎች አይመች ይችል ይሆናል ግን እንደ ኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች አይጎረብጥም፤ ከብዙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የተሻለ አኩርፈንው እንኳን እንቅፋት አይንካህ የምንለው መሪ ነው፡፡ እንዲህ ባለው መሪ እንኳን የቀጣይ መስከረም የምጽአቱ መስከረም ክተት መጥራት ጉንጭ ማልፋት ነው፡፡ እኛ ጠንካራ ሀገር ሁሉ እኩል የሚኖርባት እንድትኖረን እንመኛለን፡፡

እጣ የወጣልንን ኮንዶሚኒየም ሊነጥቅ የሞሞክር ጨካኝ ነገን መሪ ለመሆን ሲያዛጋ ጉሮሮ ውስጥ የሚገባ ሞኝ ያለ አይመስለኝም፡፡ እኔ አሁን ከብልጽግና ቀጥሎ ምረጪ ብባል ህወሃትን እመርጣለሁ እንጂ ሀገሬ ተቃዋሚ አላት ብዬ ድምጼን ተስፋዬን ቀርጥፎ ለሚባል ቡድን አልሰጥም፡፡ ሀሳባችሁን በኢትዮጵያዊነት ጨዋነት አጋሩን፤ እውነት የማያውቁት ሀገር ይናፍቃል? የምርጫስ ናፍቆት አለን?

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top