Connect with us

የኤልሳቤት ከበደ ጉዳይን በተመለከተ…

የኤልሳቤት ከበደ ጉዳይን በተመለከተ…
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የኤልሳቤት ከበደ ጉዳይን በተመለከተ…

የኤልሳቤት ከበደ ጉዳይን በተመለከተ…

(ቆንጅት ተሾመ)
“ጉዳዩ ወደ ፌዴራል እንዲመጣ አድርገናል፡፡ የተፈጸመውንም የመብት ጥሰት እናጣራለን” ብለዋል የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህጓ አዳነች አበቤ…ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ!

እሳቸው ይህንን ቢሉም አሁንም ኤልሳቤት አሁንም ሐረር እስር ላይ ናት!
ይህንንም አሳፋሪ የባለስልጣናት አፈና በማሳወቅ ተባበሩን!

የህግ ባለሞያዋን የኤልሳቤት ከበደን ጉዳይ በተመለከተ በቅርበት በመከታተል ከሚገኙ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከሳምንት በፊት ለሐረሪ ክልል ለሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ትዕዛዝ በመስጠት ሀላፊነቱን ቢወጣም የሐረሮቹ የኤልሳቤት አሳሪዎች ተፋጻሚ አላደረጉም!

ኤልሳቤት በአፈና መልክ ከምትኖርበትና ከምትሰራበት ከአዲስ አበባ ከተማ ተወስዳ ከታሰረች አንድ ወር አልፏታል፡፡
ለሐረሮቹ የኤልሳቤት አሳሪዎች ልጅቷን የወሰዱበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነ ተገልጾላቸው፤ ጉዳይዋን በምትኖርበትና በምትሰራበት ከተማ በአዲስ አበባ የመከታተል መብቷን እንዲያከብሩ ደብዳቤ ከተጻፈላቸው ሳምንት እንዳለፈ ሰምተናል፡፡

ኤልሳቤት ዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን በነበራት መደበኛ ቀጠሮ ሐረር ፍርድ ቤት ስትቀርብ ‹‹ጉዳዬን ሐረሪ ክልል ላይ አልከላከልም፡፡ ከፌዴራል የተጻፈው ደብዳ ተፈጻሚ ይሁንልኝ” ብላ ነበር፡፡

ተሰይመው የነበሩት ዳኛዋም “የምን ደብዳቤ.. ደብዳቤውን አምጪው…” ብለዋታል፡፡ (በሚያሳዝን ሁኔታ ደብዳቤው ኤልሳቤት እጅ እንዳልሆነ ያውቃሉ፡፡ እሳቸውም እንዳዩት ሰምተናል፡፡)

አሁንም የኤልሳቤት አሳሪዎች… የፌዴራል መንግስት ትዕዛዝን በአስቸኳይ ተግባራዊ አድርጉ!…

ፍትህ ለፍትህ ጠያቂዋ ለኤልሳቤት ከበደ!

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top