Connect with us

ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓታት 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋገጠች

ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓታት 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋገጠች
Sudan's Minister of Health Akram Ali Altom speaks during a Reuters interview amid concerns about the spread of coronavirus disease (COVID-19), in Khartoum, Sudan April 11, 2020. REUTERS/Mohamed Nureldin Abdallah

ማህበራዊ

ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓታት 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋገጠች

ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓታት 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ አረጋገጠች፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን እና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ወደ 592 ማሻቀቡን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት አምስት ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን ማጣታቸውንና የሟቾቹ ቁጥር ወደ 41 ከፍ ማለቱ በሪፖርቱ አሳይቷል፡፡ ስድስት ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገሙ ሰዎች ቁጥር በሱዳን 52 ደርሷል፡፡

በሀገሪቱ ካሉ 18 ግዛቶች በ14ቱ ቫይረሱ መከሰቱን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አረጋግጧል፡፡ በቫይረሱ ከፉኛ በተጎዳችው ርእሰ መዲናዋ ካርቱም ቫይረሱን ለመቆጣጠር ፖሊስ ርምጃ እየወሰደም ነው ተብሏል፡፡

በከተማዋ በሚገኙ 200 መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ 1ሺህ 365 ተጨማሪ የፖሊስ አባላትን ማሰማራቱንም የሀገሪቱ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዑመር አብዲል ማጂድ ተናግረዋል፡፡

በሱዳን የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ካለፈው ሚያዚያ 10/2012ዓ.ም ጀምሮ የእንቅስቃሴ እገዳ መጣሉ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top