Connect with us

ባንክ ለመዘረፍ የሞከረው ሰራተኛ ከእነግብራበሮቹ ተያዘ

የሚጠብቀውን ባንክ ለመዘረፍ የሞከረው ሰራተኛ ከእነግብራበሮቹ ተያዘ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ባንክ ለመዘረፍ የሞከረው ሰራተኛ ከእነግብራበሮቹ ተያዘ

ከሁለት ግብራበሮቹ ጋር በመሆን የሚጠብቀውን ባንክ ለመዘረፍ የሞከረው የጥበቃ ሰራተኛ ከእነግብራበሮቹ እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ወንጀሉ የተፈፀመው ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ/ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከሚገኘው ህብረት ባንክ መስቀል ፍላወር ቅርጫፍ ነው፡፡

በአንድ የጥበቃ አገልግሎት በሚሰጥ ድርጅት ተቀጥሮ የሚሰራ የጥበቃ ሰራተኛ ተረኛ መሆኑን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም አስቀድሞ ከሁለት ግብረ አበሮቹ ጋር በመነጋገር ወንጀሉን መፈፀማቸውን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዩን ኃላፊ ኮማንደር ጋሻው ፅጌ ገልፀዋል፡፡

የጥበቃ ሰራተኛው የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ሁለት ግብራበሮቹን በር ከፍቶ በማስገባት አብሮት ተረኛ የነበረውን የጥበቃ ሰራተኛ በማሰር እና በመሳሪያ በማስፈራራት ገንዘብ የሚቀመጥበትን ካዝና ለመስበር ሲታገሉ ታስሮ የነበረው የጥበቃ ሰራተኛ የራሱን ዘዴ ተጠቅሞ በማምለጥ ከባንኩ በመውጣት ያሰማውን ጩኽት የሰሙና በስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ደርሰው ሦስቱንም ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ተራውን ጨርሶ ጎኑን ባሳረፈበት አጋጣሚና ባልጠበቀበት ሁኔታ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ለጥበቃ ስራ የተሰጣቸውን መሳሪያ በመጠቀም እንዳስፈራሩትና ለወንጀሉ ተባባሪ ካልሆነ ለመግደል እንደዛቱበት ያስረዳው ወንጀል ፈፃሚዎቹ እንዲያዙ ያደረገው የጥበቃ ሰራተኛው አቶ ተመስገን ከሮ ነው፡፡

አብሮት የሚሰራው ጓደኛው ከሌሎች ጋር ተባብሮ ወንጀል ይፈፅማል ብሎ እንዳልገመተ እና በወቅቱ ከፖሊሶች ጋር በመቀናጀት ወንጀል ፈፃሚዎቹን መያዝ እንደተቻለ አስረድቷል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀሉን ለመፈፀም የተጠቀሙበት ልዩ ልዩ መሰርሰሪያ ብረቶች በኤግዚቢትነት መያዙን እና ከዚህ የወንጀል ድርጊት መረዳት የሚቻለው አብዛኛው የጥበቃ ሰራተኞች የተጣለባቸው ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት እንደሚያደረጉ እና ጥቂቶች ደግሞ ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው ከወንጀል ፈፃሚዎች ጋር በመተባበር መሰል ወንጀል እንደሚፈፅሙ ተቋማት ተገንዘበው በአስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኮማንደር ጋሻው ፅጌ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ እንዲያዙ ሙያዊ ኃላፊነቱን ለተወጣው የጥበቃ ሰራተኛ እና ለፖሊስ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ:- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top