Connect with us

ኢትዮጵያ የመጣው የቻይና የሕክምና ልዑክ ሥራውን አጠናቀቀ

በኢትዮጵያ እርዳታ ለማድረግ የመጣው የቻይና የሕክምና ልዑክ ሥራውን አጠናቀቀ
Photo: Social media

አለም አቀፍ

ኢትዮጵያ የመጣው የቻይና የሕክምና ልዑክ ሥራውን አጠናቀቀ

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከቻይና የመጣው የሕክምና ልዑክ ቡድን ሥራውን አጠናቀቀ።

የኮሮናቫይረስ ለመከለካል ቻይና ወደ ኢትዮጵያ የላከችው የጤና ባለሙያዎች ልዑክ ቡድን ትናንት ሥራውን አጠናቆ በጤና ሚኒስትሯና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር አሸኛኘት ተደርጎለታል።

12 የጤና ባለሙያዎችን የያዘው የልዑክ ቡድኑ የኮሮናቫይረስ ለመከላከል ላለፉት ሁለት ሳምንታት የተለያዩ የህክምና ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል።

የልዑክ ቡድኑ የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች፣ የመተንፈሻ አካላት፣ የኢንፌክሽን በሽታንና ጽኑ ሕሙማን የሚያክሙ እንዲሁም የላቦራቶሪ ባለሙያዎችን የያዘ ነበር ተብሏል።

የልዑክ ቡድኑ ካደረገው የሕክምና እርዳታ በተጨማሪም ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕክምና ግበዓቶችን ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።

ቻይና ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ባላት ልምድ ላይ ለበርካታ የጤና ባለሙያዎችና ተቋማት የልምድ ልውውጥና ውይይት ማድረጉም እንዲሁ።

የሕክምና ልዑክ ቡድኑ አባላት ጎን ለጎንም የኮሮናቫይረስ ሕሙማን የሚገኙበትን ሆስፒታልና የተዘጋጁ ሆስፒታሎችን በአካል በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለሙያዎቹ በቆይታቸው የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚደረገው ሥራ በመደገፍ ትልቅ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የጤና ቡድኑ እገዛ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን አጋርነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመው አጋርነቱ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የልዑክ ቡድኑ እንዲሁም የቻይና መንግስት በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት እስካሁን ላደረጉት ድጋፍም ሚኒስትሯ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን በበኩላቸው “ቻይና የህክምና ልዑክ ቡድን ወደኢትዮጵያ የላከችው አገራቱ ባላቸው ወዳጅነት ነው” ብለዋል።

ይህም የሁለቱ አገራት የረጅም ዓመት ስትራቴጂካዊ አጋርነት አመላከች መሆኑን ጠቁመው ቡድኑም ተልዕኮውን በተሳካ መልኩ ማጠናቀቁን ገልጸዋል።

ይህም አጋርነት ወደፊት ሁኔታዎች እየታዩ እንደሚጠናከሩ አምባሳደር ታን ጂያን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ሥራውን ያጠናቀቀው የቻይና የሕክምና ቡድን ቀጣይ መዳረሻውን ጂቡቲ ያደርጋል ተብሏል።

ምንጭ:- ኢዜአ

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top