Connect with us

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው 53 በመቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው 53 በመቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ተገለፀ
Coronavirus quarantine (Source: MGN)

ጤና

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው 53 በመቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ አብዛኞቹ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ አብዛኞቹ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታወቀ ፡፡

ከመጋቢት 4 ፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ 131 ሰዎች ውስጥ 69 ያህሉ በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ከነበሩ መንገደኞች ውስጥ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይህም 53 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ ነው ኢኒስቲትዩት ያስታወቀው ፡፡

በአየር እና በየብስ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ማንኛውም መንገደኛ ለ14 ቀናት በተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ የሚቆዩና ጊዜያቸውንም ሲያጠናቅቁ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እየተደረገላቸው እንደሚወጡ ያስታወቀው ተቋሙ፣ እስከዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ እና በክልል ከሚገኙ የለይቶ ማቆያ ቦታዎች በተገኘው መረጃ መሰረት ከ16 ሺህ በላይ ከውጭ ሀገር ተመላሾች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የ14 ቀን ቆይታ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እና የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከኮሮናቫይረስ ነጻ የሆኑ 5342 ሰዎች ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉንም ኢኒስቲትዩቱ አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደገለጹት በሀገራችንም ማንኛውም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ መንገደኛ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲገባ በማድረግ ሂደት በቫይረሱ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ማግኘት ተችሏል፣ ይህም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እገዛ ማድረጉን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

መንገደኞች በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ መደረጉ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን በመረዳት በማቆያ ውስጥ በሚሆኑበትም ወቅት ከሌሎች ጋር ባለመገናኘት ራሳቸውን እንዲጠብቁ እና ወደ ቤተሰቦቻቸውም ሲቀላቀሉ ለህብረተሰቡ የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መልዕክት እንዲያስተላልፉ አቶ አስቻለው አባይነህ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top